Ethiopian Farmers >
Interviews >
Azmach Feseha Zewde, Sami Haji Aman, Tore Neguse, Azmach Kasa Woldeyohanes, and Teruneh Walde Interview

Audio File:
Download File: Download
Download File: Download
Transcript:
Open/Close
ዛሬ እዚህ የተሰባሰባችሁት እሳቸው ፕሮፌሰር ጌትነት በቀለ ይባላሉ ለምን እንደመጡና ከየት እንደመጡ ራሳቸውን በማስተዋወቅ ጀምረው ግብርናውን መሠረት ያደረገ ጥያቄዎች ያቀርቡላችኋል እናንተም የምታውቁትን በሙሉ በዝርዝር እንድትገልፁላችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ ህጋዊ የሆነ መረጃ ለመሰብሰብ ፈቃድ አግኝተው የመጡ ሲሆን በክልል ደረጃም ፈቃድ ተሰጥቷቸው ከጉራጌ ዞን የኛ ወረዳ የተመረጠ በመሆኑ ነው ወደዚህ የመጡት አሁን እሳቸውን ስሟቸው
እኔ ጌትነት በቀለ እባላለሁ የመጣሁት ከአሜሪካን ሀገር ነው ዓለም ባንክ ኦክላንድና ሚሽጋን ዩኒቨርስቲዎች የአካባቢ የአየር ሁኔታንና የአየር ብክለትን እንዴት መቋቋም እንችላለን እና የገበሬ የአኗኗር ሁኔታ በምግብ በእርሻ የሚለውን በተለያየ ሳይንሳዊ መንገድ ጥናት ቢደረግም የገበሬውን ሃሳብ ስላላገኘን ጥናቱ ሙሉ ስለማይሆን አሁን እናንተን ለማናገርና ጥናታችንን ሙሉ ለማድረግ ነው፡፡ እኔ ጥያቄዎች አቀርባለሁ እናንተ የምታውቁትን ከቀደመውም ጊዜ ጀምሮ አስከአሁን የምታውቁትን ታስረዱኛላችሁ፡፡
በቅድሚያ እኔ እንዳደረኩት ስምና ዕድሜያችሁን እዚህ አካባቢ ምን ያሀል ጊዜ እንደኖራችሁ ትገልፁልኝና ጥያቄአችንን እንጀምራለን፡፡
1. አዝማች ፍስሀ ዘውዴ የተወለድኩት በድሮ ሸዋ ክ/ሀገር ሜታ ሮቢ ወረዳ ነው ከ194ዐ ጀምሮ እዚህ ማረቆ ነው የምኖረው
2. ሀጂ አማን ዕድሜ 38 የተወለድኩት ስልጢ ወረዳ ዶዶሎ በር የሚባል ቀበሌ ነው በህፃንነቴ በ1963 ዓ.ም ነው ከቤተሰብ ጋር ወደዚህ የመጣሁት ትምህርት ጀምሬ ነበር ሆኖም ብዙ አልገፋሁበትም አሁን በግብርና ነው እየተደደርኩት ያለሁት
3. ሜንጦሬ ንጉሴ እባላለሁ የተወለድኩት ሰሜን ዲዳ ቀበሌ ነው በጋብቻ ነው ወደዚህ የመጣሁት ስምንት ልጆች አሉኝ የምተደደረው በግብርና ነው
4. አዝማች ካሣ ወ/ዮሐንስ የተወለድኩት ሶዶ ወረዳ ነው በ1946 ነው ወደዚህ የመጣሁት የምተዳደረውም በግብርና ነው፡፡
5. ስሜ ጥሩነሽ ወልዴ የተወለድኩት ቡታጅራ መስቃን ወረዳ ሲሆን በልጅነቴ ማረቆ ገብቼ እዚሁ ነው የምኖረው
6. መርጋ አሰፋ የተወለድኩት በ1958 ነው የምተዳደረው በግብርና ነው እስከ 6ኛ ክፍል ተምሬ አለሁ፡፡
አሁን ራሳችሁን አስተዋውቃችኋል ወደ ጥያቄ እንገባለን፡፡
ጥ. የመጀመሪያ ጥያቄ ለአቶ አዝማች ፍስሀ አቀርባለሁ ለ6ዐ ዓመታት እዚህ አካባቢ ኖሬአለሁ ብለዋል? እንዴት ነው እዚህ አካባቢ ምን አዲስ ነገር አለ ከድሮው ጋር እያነፃፀሩ ቢነግሩኝ?
መ. እዚህ አካባቢ ስኖር ብዙ ልጅ ወልጄ እስከ ቅድምአያት ደርሻለሁ ዘሬም እስከ 63 ደርሷል፡፡ ልጆቼ ግማሾቹ ተምረዋል የተወሰኑትም በግብርና ላይ ነው ያሉት፡፡
ከ194ዐ-2ዐዐ2 ድረስ በእርሻና በተለያዩ ሥራዎች ነው የኖርኩት አብዛኛው ስራዬ እርሻ ነው አርሳለሁ አደግ ብዬ ወደ ደህና ሰዎች ለመጠጋት ስፈልግ ደርግ ብቅ ብሎ ትንሽም ያለውን ብዙም ያለውን ሙልጭ አድርጎ ወርሶ እኔም ያሉኝ መሬቶች ተወርሰው አድሀሪ ነው ተባልኩ በዚህ ሁኔታ እያለን ኢህአዲግ ገባ በእኔ በኩል የነፃነት መንግስት ነው እለዋለሁ፡፡ ሀብት ባገኝም ባላገኝም ነፃነት አለ ችግርንም ለፈለጉት ባለስልጣን የማቅረብ መብት አለ መልስ ቢገኝም ባይገኝም በእርሻው ያለው ሁኔታ አሁን በጣም ጥሩ ነው በ2ዐዐ1 ዓ.ም. ድርቅ ነበር ዘንድሮ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ዘነበ በግብርና ሠራተኞች ክትትል ጥሩ እሸትና ቃሪያ አግኝተናል የካቲት 19-23 የተዘራ ሽንኩርት መጋቢት ግማሽ ላይ ደርሶ ተሸጧል መንግስት ወይም የአካባቢው ባለስልጣን ገበያ አፈላልጎ ባያገኝም በተባባሪ ነጋዴ ሽጠናል በተለያየ ዋጋ
ጥ. በዚህ ዓመት እርሻው ጥሩ የሆነው የዝናቡ ሁኔታ መስተካከሉ ነው ብለዋል ይሄ ዋና ምክንያት ይመስልዎታል?
መ. ዋናው ዝናቡ ነው ምንም እርዳታ ቢደረግ ዝናብ ከሌለ ዋጋ የለውም
ጥ. በእርስዎ ዕድሜ የገበሬው የስራ ሁኔታ /ህይወት/ የሚወሰነው በመንግስት ፖሊሲ ነው ወይንስ በዝናቡ?
መ. የተለያየ ነው አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይሰጣል በመንግስት መሟላት ያለባት ሳይሟላ ይቀርና ምርቱ ይቀንሳል፣ አንዳንደ ደግሞ በመንግስት የሚሟላው የሟላና ዝናቡ ይጠፋል፡፡ በእርግጥ የግብርና ባለሙያዎች በጣም ነው የሚረዱን እርሻችን ድረስ እየመጡ ነው እርዳታ የሚያደርጉልን፡፡
ጥ. እርስዎ እስኪ እንደት ወደ ግብርና እንደገቡ እና ባጠቃላይ ስለ ስራዎት ቢያስረዱኝ?
መ. እኔ በ1986 ነው እርሻ የጀመርኩት ወረዳችን በድህነት ተጠቃሽ ናት ህብረተሰቡ የግንዛቤ ችግር ነበረበት መንግስት እስከ መቼ ነው የሚረዳው በሚል አሁን ግብርና ሚ/ር ባለሙያም እየረዱን አየሩም ጥሩ ስለሆነ በደንብ እየሠራን ነው፡፡
ጥ. በፊት ተማሪ ነበርክ መሬት ከቤተሰብ ነው ወይስ ከየት አገኘህ?
መ. አባቴ ሲያረጁ ትምህርቴን አቋርጨ አባትና እናቴን ለመጦር መጣው የነሱን እየሰራሁ ሳገባ ከአባቴ ተካፈልኩኝ በመጨረሻ አባቴ ሲሞቱ መሬቱን ጠቅልዬ ያዝኩኝ፡፡
ጥ. እርሻ የወንድ ነው ይባላለ በዚህ ሃሳብ እርስዎ ይስማማሉ?
መ. አልስማማም ሴቷ ብቻዋንም ከሆነች ለራሷ ታርሳለች፡፡ ባለቤት ካላትም አብራ ትሰራለች ስለዚህ የወንድ ስራ አይደለም፡፡
ጥ. ያላችሁበት መሬት የማንነው የእርስዎና የባለቤትዎ የጋራ ነው ብለው ያምናሉ ወይም የባለቤትዎ ብቻ?
መ. የጋራ ነው አሁንማ ዘመኑ ተሻሽሎ ወንዱም ሴቱም እኩል መብት አለው፡፡ የአባቴን ንብረት እንኳን ከወንድሜ ጋር እኩል እካፈላለሁ፡፡
ጥ. ሴት ልጅ አለዎት ካለዎት እንደርስዎ ይድሯታል?
መ. እንኳን የራሴን ልጅ በአካባቢው ያሉ ሴት ልጆች እንዳይዳሩ እመክራለሁ፡፡
ጥ. በዚህ አካባቢ በብዛት ማሳ ላይ በብዛት የሚመረተው ምንድን ነው?
መ. በዚህ አካባቢ መሬቱ ለምነው ስንዴ፣ በቆሎ፣ በርበሬ፣ ሽንኩርትና የመሳሰሉት ይመረታሉ
ጥ. የእነዚህ ምርቶች ዘራቸው ከየት ነው የመጣው?
መ. በርበሬ ከጥንት ጀምሮ ነው የማረቆ በርበሬ፣ የታወቀም ነው ሽንኩርት በቅርብ ነው የመጣው
ጥ. ሽንኩርት በደርግ ዘመን ነው የመጣው?
መ. በኢህአዲግ ነው
ጥ. በቆሎስ?
መ. እሱ ከጥንት ጀምሮ ነበር
ጥ. ከበርበሬና በቆሎ የቱ ነው የቀደመው ይባላል?
መ. እኩል ናቸው
ጥ. ስንዴስ?
መ. ስንዴ አዲስ ገቢዎቹ ናቸው ያስፋፋቱ በፊት ብዙም አይመረት ነበር አሁን ጥቅሙ ስለታወቀ በስፋት ይመረታል
ጥ. ማሽላ እዚህ አካባቢ ተመርቶ ያውቃል?
መ. ማሽላ ሁለት ዓይነት ነው ያለው ዘንጋዳ ድሮም ይዘራል
ጥ. ድሮ ሲሉ ከበቆሎ ጋር እኩል ነው?
መ. አዎ እኩል ነው
ጥ. ለምን ይመስልዎታል ሰው አንዱን አዝመራ መርጦ የሚዘራው እርሱ ስለሚዘሩት እህል ያስባሉ?
መ. አዎ አስባለሁ ለምሳሌ በርበሬና ሽንኩርት በክረምት ገንዘብ መጨበጫ ስለሆነ ለገንዘብ ተብሎ የሚዘራ ነው፡፡ ስንዴ ለሁለቱም ለቀለብና ለገንዘብ ተብሎ ይዘራል በገንዘቡ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ይሟላበታል በአብዛኛው ግን በቆሎና ስንዴ ቀለብ ነው፡፡
ጥ. ሴት በማረሷ ይስማማሉ?
መ. አዎ ሞፈርና ቀንበር ባልይዝም ገበሬዬን ተከትዬ እኮተኮታለሁ አርማለሁ እንዲያውም ከ4 ዓመት በፊት ሌላ ቦታ ለውዝ ተክለው አይቼ ገዝቼ አምጥቼ ዘርቼ ስከታተል መንገደኛው እየመዘዙ አውጥተው ጨረሱት፡፡
ጥ. እንዴት ሞከሩት በአካባቢው አለ?
መ. አዎ ያመረተ አለ የኔም የተወሰነ ደረጃ ከደረሰ በኋላ ልጆቹ /እረኞቹ/ መዘው አውጥተው አበላሹብኝ፡፡
ጥ. የተወለዱት እዚሁ አካባቢ ነው?
መ. ቡታጅራ ነው የተወለድኩት፡፡
ጥ. አካባቢውን ከልጅነትዎ ጀምሮ የሚያውቁት ከሆነ ምን የተቀየረ ነገር አለ?
መ. ውሃ ከወንዝ ነበር በእንስራ የምናመጣው አሁን በየደጃችን ሆኖልናል
ጥ. እርሻውስ ላይ ምን ለውጥ አለ?
መ. ብዙ ለውጥ አለ ድሮ የሚዘራው ትንሽና አልፎ አልፎ ነው ከብት ነበር የነበረው አሁን መሬቱ በሙሉ ታርሶ አንድ ቦታ የለም ከብትም የለ
ጥ ይሄ ሊሆን የቻለው በምን ምክንያት ነው? ሰው ከብት ማርባት ለምን ተወ ወተት ስላልፈለገ ነው መሬቱ በሙሉስ ለምን ታረሰ በምን ተገዶ ነው?
መ. ከከብት ጥቅም የእርሻ ጥቅም ስለሚሻልና የቦታ ጥበትም ስላለ ነው
ጥ. ከብት የነበረበት ዘመን ላይ ደርሰዋል?
መ. አዎ ደርሼበታለሁ የአባቴን አግጃለሁ
ጥ. አባትዎ ምን ያህል ከብት ነበራቸው?
መ. 55 ነበራቸው
ጥ. እርስዎ ምን ያህል ከብት አለዎት?
መ. አባቴ ሲሞቱ ሃላፊነቱ ወደ እኔ ዞረ የእናቴን ከብት እያገድኩ እናቴን እጦር ጀመር 1 ሄክታር መሬትም አለኝ
ጥ. ምንድነው ማሳዎ ላይ የሚዘሩት?
መ. በርበሬ ነው ለኔ ትልቅ ጉልበት የሰጠኝም በርበሬ ነው ብዬ መናገር እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ስንዴ ሽንኩርት እተክላለሁ፡፡ ሰንዴ ምርጥ ዘር እዘራለሁ ከቀለብ አልፌ እሸጣለሁ፡፡
ጥ. አሁንስ በርበሬ ይተክላሉ ትተዋል?
መ. አዎ ትቻለሁ፡፡ በሽታ ገብቶ ከተበላሸ በኋላ
ጥ. እዚህ አካባቢ ጭራሽ እርሻ አልነበረም ነበር ይባላል ይሄ እውነት ነው?
መ. አዎ ከብት በነበረበት ዘመን አልፎ አልፎ ነው የሚዘራው እንጂ እርሻ ዋና ስራቸው አልነበረም በርበሬ ብቻ ነው የሚተከለው አካባቢው በጣም ደን ነበረው አሁን የደኑ መመንጠር ይመስለኛል የአየር ሁኔታው የተቀየረበት
ጥ. ደኑ በብዛት ምን ዓይነት ነበር?
መ. ግራር ሀረግ የሚመስልና የተለያየ ነበር
ጥ. ደኑ የማን ነበር?
መ. የሠፈረው ህዝብ ነው የኛ ነው ብሎ ይንከባከበው ነበር ይጠብቅ ነበር መንግስት ብዙም ትኩረት ስላልሰጠና ስለማይከታተል ተጨፍጭፎ አለቀ
ጥ. ማን እየፈቀደ ነው ደኑ እየተጨፈጨፈ አዝርዕት ከተዘራ የጋራ የነበረው የግል ሆነ ማለት ነው ይህንን ማን እየፈቀደ ነው?
መ. በደርግ ጊዜ በወቅቱ የነበሩት ባለስልጣን ወይም የቀበሌ መሪዎች ናቸው የሚሰጡት ከቀበሌ አመራር ከተስማማ እነርሱ ናቸው የሚሰጡት 8 ሄክታር ድረስ ይሰጥ ነበር፡፡ ያኔ ለእርሻ ትኩረት አይሰጥም ነበር፡፡ አንዱ ሠርቶ ውጤቱ ሲታይ ሌላውም ይሰጠኝ እያለ የፈለገውን ያህል ሄክታር እየመነጠረ ይወስድ ጀመር
ጥ. ስለደርግና ኢህአዲግ አውርተናል ስለ አፄ ኃ/ስላሴ ትንሽ ቢነግሩን?
መ. ጣሊያን ወጣ አፄ ኃ/ስላሴ ተመለሱ በዛን ጊዜ የባላባት አስተዳደር ነበር በዛን ሰዓት ባላባቶች ጭቃሹምና ጭሰኞች ነበሩ ያን ጊዜ እንዲያውም የጭሰኛ ጭሰኞችም ነበሩ፡፡ በዚያን ወቅት አንድ ጋሻ መሬት የነበራቸው ከዘር የተወረሰ ወይም መንግስት የፈቀደው የወል /የመንግስት/ መሬት ይበዛል ያልታረሰው ሁሉ የመንግስት ነው የሚባለው ማረቆ እኔ ከገባው ጊዜ ጀምሮ ዝም ብሎ መሬት ይሰጡኛል አርሼ እበላለሁ ሰዎቹ በጣም ጥሩ ስለሆኑ ምንም ሳልከፍል አርሼ እበላ ነበር እየቆየ ሲሄድ እርቦ መጣ አንድ እጅ ለባለ ርስት እንሰጥ ጀመር፡፡
ጥ. እርቦ የሚለው መቼ የተጀመረ ይመስሎታል?
መ. ጣሊያን ወጥቶ ከ1ዐ ዓመት በኋላ አካባቢ ይሆናል እርሶ የመጣው ከእርቦ ጋር ደግሞ አስራት መጣ ፡፡ አስር አርሼ ቢሆን 6ቱ ለራሴ ሶስት ለባለ ርስት አንድ ለመንግስት ማለት ነው ይሄን ሰጥተን ያለምንም ጭቅጭቅ አርሰህ እኖራለህ፡፡ እርሻም በብዛት አልነበረም ለምሳሌ ቀኛዝማች ሸቤ የሚባሉ ከ3ዐዐ በላይ ከብት ነበራቸው አብዛኛው ህዝብ ከብት ነበረው ከብት በፈለገበት ተሰማርቶ ውሎ ማታ ይገባል፡፡ እኔ ቦታ ላይ መጣ ብሎ መጨቃጨ የለም ምንም ችግር አልነበረም እርሶ ለምግብ ያክል ብቻ ነበር ብዙም ሽያጭ የለ በ1942 ዘንጋዳ ልትሸጥ ወጥታ አልሸጥ ሲላት እዛው ትታ የሄደች አስታውሳለሁ፡፡ በአፄ ኃ/ስላሴ በጣም ጥጋብ ነበር ደርግ መጣ ባላባት ተባረረ መሬት ተከፋፈለ ከዛ በኋላ መሬት እየተሸነሸነ ተሰጠ በዛ ነው የእርሻ ጣፋጭነት የተጀመረ፡፡ ቀጥሎ ኮታ የሚባል ነገር መጣ እኔ ለመሻሻል በጣም ስለምሠራ ያልዘራሁትን 2 ኩንታል ጤፍ ተመደበብኝ አንድ ፈረሱላ በርበሬ ለዘማች ተብሎ ሁለቱንም ጤፍም አልዘራሁም በርበሬም አልተከልኩም ስለዚህ 4 ጆንያ ስንዴ ይዤ ሄድኩኝ ይህንን አንቀበልም ብለው እምቢ አሉኝ ከዛ ሌሎች ትተህ ሂድ አሉኝ ልሄድ ስል የወረዳ ሃላፊው መጥቶ አገኘሁት እና ያመጣሁትን ኮታ ስንዴ አልቀበልም አሉኝ ስል የቀበሌው ሊ/መንበር ተጠየቀ ያልዘራውን ለምን አምጣ አልከው ተባለ የመደበው ሌላ ነው አለ ከዛ ኮታም ሳልሰጥ ስንዴዬን ይዜ ተመልሻለሁ በደርግ ያስመረረን ነገር ኮታ ነበር፡፡
ጥ. በደርግ ጊዜ ኮታ የሚባል ነገር መጥቶ ሰው መማረሩን ሰምተናል በኢህአዲግ ጥሩውን ሰምተናል መጥፎ የሚባል ካለ ቢነግሩን? እርስዎ እርሻ የጀመሩት በ1986 ስለሆነ
መ. መጀመሪያ ህዝቡ በደርግ ተሠቃይቶ የደከመ ነበር በደርግ ግን እፎይታ አግኝቷል በአሁኑ መንግስት መብት አግኝቷል ህዝቡ የያዘውን መሬት እንደያዘ ነው ያለው ገበሬው ባለመማሩ የተፈጠረ ችግር እንጂ ምንም በደል አልደረሰም፡፡
ጥ. ሴቶች መብታቸውን አውቀው ተቀይረዋል ይባላል አሁን በትክክሉ ግን እርስዎ በቤትዎም በአካባቢዎም ያሉ ወንዶች ለሴቶች ያላቸው አመለካከት ተቀይሯል ብለው ያስባሉ?
መ. የግድ ይቀየራሉ እኛም ስንተገብርና ገብተን ስናስረዳም የግድም ቢሆን እየተቀየሩ ነው፡፡
ጥ. ለምሳሌ የእርስዎ ባለቤት እኩል ነን ብለው ያምናሉ?
መ. አዎ በፊት ነበር እንጂ አሁን እኩል ነን ብሎ ያምናል
ጥ. ሴትና ወንዶች ልጆቻችሁን እኩል ነው የምታሳድጓቸው?
መ. አዎ እኩል ነው ትምህርት ይማራሉ ያው ሴቶች ልጆች ለወላጆቻቸው ስለሚያስቡ እና በአንዴ ስለማይለቅ እንጂ እኛ እኩል ነው ሁሉንም ለማድረግ የምንሞክረው፡፡
ጥ. በቤት ባለ ገንዘብ ወይም አምርታችሁ ከሸጣችሁ በኋላ በገንዘቡ ላይ እኩል የማዘዝ መብት አላት ሴቷ?
መ. አዎ ከዚህ 4 ዓመት ወዲህ እኩል ነው የምናዘው
ጥ. እርስዎ ስለጣሊያን ያውቃሉ ደርሰውበታል እንዴ?
መ. አይ እኔ አልደረስኩበትም አባቶቼ ሲያወሩ ከሰማሁት ጎጎቲና ሀሙስ ገበያ ሰፍረው እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡
ጥ. እርሻ ጣሊያን ነው እንዴ የጀመረው?
መ. አይ በአስተዳደር እንጂ በእርሻ እንኳን አልሰሩም
ጥ. ጣሊያን ግብር ማስገበር ጀምሮ ነበር እንዴ?
መ. አናውቅም
ጥ. ከጣሊያን በኋላ የባላባት ስርዓት ነበር ተብሏል? ከነበረ እስኪ ምን ዓይነት አስተዳደር እንደነበር ስለባላባቱ ቢገልፁልኝ ስማቸውን ካወቋቸው?
መ. ባላባቶቹ ቀኛዝማች ሸሸቤ አባታቸው መሴ ባከሙ ይባላሉ ባላምባራስ አሰፋ ባላባት ሆኑ ጭቃ ሹሞች ሽብሩ ዳጌ ስዩም የሚባሉ ነበሩ ዋናው አስተዳደር ባላባት ነበር፡፡
ጥ. ይሄ ስልጣን መጀመር እንዴት መጣ በዘር ነው ወይንስ በሹመት?
መ. በዘር የመጣም ነው ግን ከአንዳንድ አባቶች ስንሰማ አፄ ምኒልክ የወላይታ ዘመቻ የሄዱ ጊዜ ብርቆምን ከኔ ጋር ዘመቻ ሂድ በማለት አብረው ሄደው ሲመለሱ በዛው ሾሟቸው፡፡ ከአዋሽ በፈሰሰ ጂዶ በመለሰ የአቶ ብርቆም ንጉሴ ነው ተብሎ ሠጧቸው ይባላል፡፡ አፄ ምኒልክ የተለያየ የሆነ የሀገር መንግስት ነበር የጅማ አባ ጅፋር እንደሚባለው በየጎሳውና በየአርበኛው ይመራ ነበር፡፡ አፄ ምኒልክ አንድ ኢትዮጵያ ለማድረግ በጀመሩት ወታደራዊ ዘመቻ አርበኛው የራሱ ጦር ስለነበረው ወደኔ ተቀላቀል ሲሉ አልቀላቀልም ስለሚል በመዋጋት በማሸነፍ ወደራሳቸው ይቀላቅሉና የራሳቸውን ሰው ይሾማሉ በዚህ ነው ብርቆማ የተሾሙት እነ ሻቃ በቀለም የመጡት ማረቆም በዛን ወቅት አልቀላቀልም ብላ የነበረች ሀገር ናት አዛዥ ለጤቦ የሚባሉ እምቢ ብለው ተዋግተው ተሸንፈው ወደ ሲልጢ ሄዱ ማረቆንም ወደ ስርዓቱ ጠቀለሉ፡፡
ጥ. በዛን ወቅት የነበሩት ባላባት ማን ነበሩ?
መ. በአዛዥ ለጨቦ ቦታ ብርቆሞ ተተካ ብርቆም ባላባት ሆኖ ሲኖር እንደገና ወደ ወላይታ ያልፉና ንጉስ ጦና ይህንን መንግስት አልቀበልም በማለታቸው የጦናን ፈረሰኝ ማሸነፍ የሚችል ማነው ተብሎ ሲፈለግ ማረቆ ነው ስለተባለ ምኒልክ ሲመጡ ብርቆም ሞቶ ልጃቸው ሚሰቦ ሲያስቀብር ይደርሳሉ ሚሰቦ ከአባታቸው ቀብር ላይ የባላባትነት ሥልጣን ተሰጥቷቸው ወላይታ ለጦርነት ከአፄ ምኒልክ ጋር ሄደው የወላይታን መሪ አሸነፉ ሽልማት ተሰጥቷቸው ተሾሙ
ጥ. ሚሰቦ ፈረስ ነበራቸው?
መ. ማረቆ በፈረስ ታዋቂ ነው ያኔም የተዋጉት በፈረስ ነው፡፡ የማረቆ ሕዝብ ተዋግቶ ራሱን የሚየስከብር ህዝብ ነበር፡፡
ጥ. የማረቆ ሕዝብ ከሀድያ ጋር ይቀራረባል?
መ. አዎ ነገዳቸው አንድ ነው
ጥ. ከሲልጢ ጋርስ?
መ. መጀመሪያም ነገዱ ከሀዲያ ነው ትውልዱ የቦዬና የሚነዶ ልጆች ናቸው የሚባለው
ጥ. ሀሰን ኢንጃሞ የሚባል ሰው ታውቃላችሁ?
መ. አናውቅም
ጥ. ከማረቆ ለየት ብለው የሚኖሩ ምሁር አካባቢ አሉ እነሱ ምንድናቸው ዘራቸው?
መ. ቀቤናዎች ናቸው እነሱም የማረቆ ዘር ናቸው
ጥ. የባላባቶች ጥቅማቸው ምንድነው ደመወዝ አላቸው ወይስ መሬት ይሰጣቸዋል?
መ. ጭቃ ሹም ይሾማሉ የመንግስት ግብር ይሰበስባሉ ባጠቃላይ ኃላፊነት አለባቸው
ጥ. እንደ ዛሬ ሹመኞች ልንወስዳቸው እንችላለን?
መ. አዎ ባላባቱ ከስሩ ጭቃሹም ጭሰኛ ስላለ ከላይ ሆኖ ይህንን ያስከብራል ማለት ነው መሬትም ከሌላው በላይ ይዞታ አይዙም ለአርበኞች መሬት ሲታዘዝ ይሰጣሉ የተያዘና ያልተያዘው የሚያውቁት እነሱ ነበሩ፡፡
ጥ. ከንሴቦ በኋላ ባላባትነት ቀረ ወይስ ቀጠለ?
መ. የንሴቦ ቀጥሎ አሸቤ ነበሩ
ጥ. እሳቸው ባላባት ሆነው ነው ደርግ የገባው?
መ. ከአሳቸው በኋላ ልጃቸው ቦታውን ይዘው አንዳለ ነው ደርግ የገባው
ጥ. ቱኬ ማማ ስለሚባል ሰው ምን ታውቃላችሁ?
መ. ቱኬ ማማ የጅዶ ኮምቦልቾ ባላባት ነበሩ ኦሮሞ ናቸው፡፡
ጥ. ሴቶች በአሁኑ ወቅት መብታቸው እየተረጋገጠና እየተከበረ መጥቷል እያልን ነው በእርስዎ ግምት ወንዶች ተሻሽለዋል?
መ. አዎ ተሻሽለዋል ተቀይረዋል ወንዱም የሴትን መብት እያከበረ በመነጋገር ነው ሁሉም የሚደረገው ወንዱ እንደ በፊቱ በስልጣኑ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡
ጥ. ቅድም መሬት አለኝ ብለውኛል ያንን መሬት ቢፈልጉ መሸጥ ይችላሉ?
መ. አልችልም መሬት የመንግስት ነው መሸጥ መለወጥ አይቻልም
ጥ. መንግስት መሬቱ የራስዎት ነው እንደፈለጉ አድርጉ ቢባሉ ደስ ይሎታል?
መ. አይለኝም
ጥ. ለምን?
መ. መሬቴን ሸጨ የት እገባለሁ አልሸጥም መሬት የመንግስት ነው ይባል እንጂ ምንም የወሰደብኝ ነገር የለም እንዲያውም አስፈላጊ ነገሮችን እያሟላልኝ ነው መንግስት
ጥ. እርስዎ ጥቅሙን ስላወቁት አይሸጡም መብቱ ቢኖርስ ሰው ይሳሳታል ብለው ያስባሉ?
መ. ሁሉም የመሬት ጥቅም ስለገባው አይሸጥም
ጥ. መሬቴ ይወሰድብኛል ብለው ሰግተው ያውቃሉ?
መ. በፍፁም ሰግቼ አላውቅም
ጥ. በደርግ ጊዜ እየተለካ የተወሰነ ይወሰድ ነበር ትርፍ ነው እየተባለ ይሄ አያሳስብም?
መ. አያሳስበኝም የያዛችሁትን እንደያዛችሁ እርጉ ተብለናል የማስበው ስለግብር ብቻ ነው እንጂ ምንም አላስብም፡፡
ጥ. የሰሙት ነገር ካለ በሙሉ ወይም በከፊል ማረስ አቅቶት መሬት የተወሰደበት ካለ?
መ. የለም በፊት በደርግ ጊዜ መሬቱን ለራሱ አድርጎ ጠፍ ያሳደረ ሰው ይወሰድበት ነበር አሁን ግን እንድናለማ ብቻ ነው የምንቀሰቀሰው የምናመርተው ምርትም የራሳችን ነው መሬት ሳያርስ አንድ ዓመት ያሳለፈ ካለ መሬቱ ይነጠቃል የሚል መመሪያ ስላለ የማያርስ ገበሬ የለም
ጥ. ምን ያህል እርዳታ ታገኛላችሁ? ይጠቅማል ወይ እርዳታውስ አስፈላጊ ነው ወይ?
መ. ምናልባት እርዳታ ማለት ለህይወት ደራሽ ነው በጣም አርጅተው ጧሪ ለሌላቸው እንጂ እርዳታው ወሳኝና የምንተማመንበትና ቀጣይ መሆን የለበትም ህብረተሰቡም ወደ አቅመ ደካማና ስደተኛ እያደረገው ነው እርዳታውን ጠባቂ መሆን የለበትም የትምህርት ክህሎት ማሳደግ በዚህ መልኩ ቢሰጥ ነው፡፡
በሶስትና በአራት ዓመት በሚያጋጥም የአየር መዛባት የመስራት አቅም የሚያንሳቸው ሰዎች መጠባበቂያ ቢሆን እንዷ ለሚሠራው ህዝብ ያስፈልጋል የሚል እምነት የለንም የአየሩ ሁኔታ ጥሩ በመሆኑ ዘንድሮ በግንቦት በቆሎ በልተን አሁን ስንዴ ዘርተናል በዚህ ሁኔታ መረዳት የለብንም 2ዐዐ3 ዓ.ም.በዚሁ የአየር ሁኔታው ከቀጠለ እህል በጣም ነው የሚረክሰው ዘንድሮ ሽንኩርት ሸጠን ስንዴ ዘርተናል ችግራችን የአየሩ ሁኔታ ነው፡፡ በግብርና ስትራቴጂም ድጋፍ እየተደረገልን ነው በዚህ 4 ዓመት ውስጥ በሞተር አልምተው ትልቅ ደረጃ የደረሱ አሉ፡፡ ሞተሩ ለሁሉም ከተዳረሰ ያለዝናብ የማምረት አቅማችን ከተሟላ እርዳታ አያስፈልገንም
ጥ. በ2ዐዐ1 ድርቅ አንደነበር ነግራችሁኛል እስኪ በዛን ጊዜ ስንቶቻችሁ እርዳታ አገኛችሁ?
መ. በ2ዐዐ1ዓ.ም. ባለመመረቱ በ2ዐዐ2 ዓ.ም ችግር ስለነበር እኔ ቤተሰቤ 1ዐ ነው ግን በ3 ቤተሰብ ተብሎ ትንሽ ነገር ተሰጥቶኛል ስጦታው በቂ አይደለም፡፡ ዘንድሮ በበቂ ስላመረትን አርዳታም አንፈልግም
ጥ. የመሬት እጥረት አለብን ብላችሁ ትገምታላችሁ?
መ. ያለኝ አለኝ ያንሰኛል ብልም ከየትም አይገኝም የሌላቸውም በኮንትራት ይዘው የሚጠቀሙ አሉ ግን በአግባቡ ከሠራን መሬት አያንስም፡፡ መሬት ወደሶስት ዓይነት ነው ያለው በደርግ ጊዜ ባለስልጣን የነበሩ በስፋት ይዘዋል እስከ 4ዐ ጥማድ የያዘ አለ ከ1982 ጀምሮ ትዳር የያዙና በደርግ ጊዜ ወጣት የነበሩ ምንም መሬት የሌላቸው አሉ ስለዚህ በራሱ መሬት ያመረተውን ለራሱ የሚጠቀም ከሆነ መሬት ያንሳል እኛ አሁንም ባለን ላይ በኮንትራት ጨምረን ይዘን ነው የምንሠራው ኮንትራት መስጠት ከቀረ እኛ በጣም እንቸገራለን ቀድመው የያዙ ናቸው ተጠቃሚ የሚሆኑት፡፡
እንዲሁም ልጆቻችን መሬት የሚካፈሉት ከቤተሰብ ነው ትምህርት ከ8ኛ ክፍል በላይ ቡታጅራ ሄደው ስለሆነ ይማሩ የነበሩት ያንን ማድረግ ቤተሰብ ስለማይችል ወደ ግብርናው ይመለሳሉ፡፡ አሁን ግን እስከ አስረኛ እዚሁ መማር ተጀምሯል፡፡ ስለዚህ ከግብርና ውጭ ለሌት አማራጮችን ይፈልጋሉ እንጂ መሬት እጥረት አለ፡፡
መሬት በጣም እየጠበበን ነው እኔ ያለኝ ቤተሰብ ከነልጅ ልጅ 63 ነው ያለኝ መሬትም 3 ሄክታር ነው ልጆቼም 8ኛ ና 1ዐኛ ክፍል እየጨረሱ እቤት የተቀመጡ አሉ እነዚህ መሬት ወይም ሌላ ስልጠና አግኝተው ሥራ ካልሰሩ በቤተሰብ ላይ ጫና ናቸው ስለዚህ መሬት በብዛት የያዙም ስላሉ የመስተካከል ስራ ቢሠራ የሚል ሃሳብ አለን፡፡
ቅድም እንደተባለው 5 ጥማድ ያለ አለ 5ዐ ጥማድ ያለው አለ እነዚህ ሰዎች ግን 5 እና 4 ሚስት አላቸው ከእያንዳንዱ ሚስት 9 እና 1ዐ ይወልዳል ስለዚህ እነዚህ ሰዎችም አከፋፍለው ባዶ እጃቸውን ነው ያሉት ስለዚህ ስራ መፍጠሩ ነው ጥሩ፡፡
ጥ. ስለ ቱኬ ማማ የሚያውቁትን ቅድም እናገራለሁ ስላሉ ቢነግሩኝ?
መ. ቱኬ ማማን አውቃለሁ ከቀኛዝማች ሸቤ ጋር አንድነት ፈጥረው ቱኬ ማማ የኦሮሞ ባላባት የኮምቦልቾ ቀኛዝማች ሸቤ የማረቆ በመሆን ተባብረው በሕዝቦቹ መካከል ፀብም ሲፈጠር ያስማሙ /ያስታርቁ/ ነበር፡፡
ጥ. ስልጢ ባላባት ነበረው?
መ. ቀኛዝማች ሻምሮ የሚባሉ ባላባት ነበሩ
ጥ. የነሱም በቤተሰብ ነው ሲዋረድ የመጣው?
መ. አዎ
ጥ. የአንዱ ባላባት የሌላውን አይነካም?
መ. አይነካካም ሁሉ በወሰኑ ብቻ ነው
ጥ. ጂዴ ትክክለ ቦታው የት ነው?
መ. ቡልቡላ ዋናው የሻሸመኔ መንገድ ላይ ነው ህፃናት አምባ
ጥ. የማረቆ ባላባት የት ነበር የሚቀመጡት?
መ. እዚሁ ማረቆ ቆሼ ነበር የሚኖሩት
ጥ. ቆሼ ነበረች ዋና ከተማ የባላባት
መ. ቆሼ ከ194ዐ እስከ 1944 አውራጃ ነበረች ሻለቃ አስፋው ገ/አምላክ አውራጃ አስተዳደሪ ቀኝአዝማች አፈወርቅ የፍርድ ቤት አዛዥ ቀኛ ሼቤ ሚሴቦ ዋና ባላባት በስራቸው 17 ጭቃ ሹም ነበራቸው
ጥ. ደብዳቤ በማምጣት መሬት የወሰዱ ሰዎች ብዙ ናቸው እዚህ አካባቢ
መ. አዎ ከ4ዐ በላይ ይሆናሉ ብዙ ናቸው
ጊዜያችሁን ከኔ ጋር በመሆን ለሰጣችሁ መረጃ አመሰግናለሁ፡፡
1

Transcript: Download (244 KB)
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Zewde, Azmach Feseha
Aman, Sami Haji
Neguse, Tore
Woldeyohanes, Azmach Kasa
Walde, Teruneh
Aba, Margasa
Bekele, Getnet
Aman, Sami Haji
Neguse, Tore
Woldeyohanes, Azmach Kasa
Walde, Teruneh
Aba, Margasa
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
- Individual life narratives
- Factors affecting agricultural production
- Farming in the post-Derg era
- Impact of modern inputs on farm production
- Interview conducted in Koshe, Maraqo, southeast of Buta Jira town, Lake region, Ethiopia
Date: August 20, 2010
Location: Koshe, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University