Bete Debele and Alamu Dabi Interview
Audio File:
Download File: Download
Download File: Download
Transcript:
Open/Close
እኔ ፕሮፌሰር ጌትነት በቀለ እባላለሁ እናንተም እራሳችሁን አስተዋውቃችሁኝ ወደ ጥያቄ እንገባለን፡፡
1. ለኬ ደምሴ እባላለሁ ነዋሪነቴ በኤጄርሶ ጅሩ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው ከሀገር ውጭ ለጥናት የተፈለገውን ነገር ከኛ በፊት ከአባቶቻችን ጊዜ ጀምሮ ያለውን የምናውቀውን ለመግለጽ እሞክራለሁ፡፡
2. አለሙ ጣአ እባላለሁ በድርጅት ሥራ እሠራለሁ
3. ረጋሣ እባላለሁ በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ ነኝ የልማት ቡድን ፀሐፊ ነኝ
ጥ. እዚህ አካባቢ ገበሬዎች የሚያመርቱት እህል ምንድነው ?
መ. ጤፍ ነው በአንደኛ ደረጃ በሁለተኛ ደረጀ ቦሎቄ በሶስተኛ ደረጃ ስንዴ
ጥ. ጤፍ መቼ ነው የሚዘራው?
መ. ከሐምሌ 5 እስከ ሐምሌ 29 ድረስ
ጥ. መቼ ይታጨዳል?
መ. አጨዳው ከጥቅምት 15 ጀምሮ ሲሆን እንደመሬቱ ሁኔታ ይለያያል
ጥ. ቦሎቄስ መቼ ይዘራል?
መ. ከሰኔ 15 ጀምሮ ይዘራል
ጥ. መቼ ይታጨዳል?
መ. ከመስከረም 17 በኋላ ይታጨዳል
ጥ. ስንዴስ?
መ. ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 2 መዘራት አለበት
ጥ. ታዲያ ገበሬዎች ለጤፍ፣ ለቦሎቄ፣ ለስንዴ ብለው የተለያየ መሬት አላቸው ወይንስ አንዴት ነው የሚዘሩት?
መ. እርሻው የቦሎቄና የስንዴ ከፍተኛ /ዳገታማ/ ውሃ መቋጠር የማይችለው ይዘጋጃል ለጤፍ ደግሞ ውሃ መቋጠር የሚችለው ተመርጦ ይዘጋጃል፡፡
ጥ. ጤፍ መጀመሪያ እዚህ አካባቢ ማን ማረስ አንደጀመረ ይታወቃል?
መ. አናውቀውም ድሮ አባቶቻችን ጤፍ በትንሹ ነበር የሚዘሩት በቆሎ ነበር የሚያመርቱ ለከብት ምግብነትም ስለሚያገለግል ድሮ ከአንድ ሄክታር በላይ አይዘራም ነበር በአሁኑ ወቅት ጤፍ አለህ ማለት ባንክ ገንዘብ አለህ ማለት ስለሆነ ሁሉም ጤፍ የሚያመርተው፡፡
ጥ. ገበሬዎች ያመረቱትን ጤፍ እንጀራ ይመገባሉ ወይንስ ለገበያ ብቻ ነው?
መ. አብዛኛው ለመሸጥ ነው የሚጠቀመው ጤፍ ነጭ፣ ሠርገኛና ቀይ ጤፍ አለ ቀይጤፍ ለቀለብ ነው ነጭና ሠርገኛው ለገበያ ነው
ጥ. ጤፍ በብዛት እዚህ አካባቢ ማረስ የተጀመረው መቼ ነው በደርግ ዘመን ነው ወይስ በኢህአዲግ በግምት ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?
መ. በኢህአዲግ ዘመን ነው በደርግ ጊዜ በማህበር ስለሚታረስ የግል ስላለነበረ የተመረተውንም ምርት እኩል ስለምትከፋፈል ጤፍ አይዘራም ኮታም ስለነበረ 2ዐ ኩንታል ጤፍ ብታመርት 1ዐ ኩንታል ይወሰድብሀል ስለዚህ ጤፍ ማምረት አይፈለግም፡፡
ጥ. ቦሎቄና ስንዴ ዕድሜው ስንት ይሆናል?
መ. ቦሎቄ አንደአየሩ ሁኔታ ነው ለምግብነት አንጠቀምበትም ስለዚህ እንደዋጋው ነው የምናርሰው ስራው ቀላል ነው ተባይም አይበዛበትም፡፡ ስለዚህ ቦሎቄ እንደዋጋው ሁኔታ ነው የምታርሰው፡፡ ስንዴ በአብዛኛው እዚህ አካባቢ አይታረስም ነበር፡፡ አሁን ግን በኢህአዲግ ጥናት ተደርጎ እዚህ አካባቢ ፋሚሊ የሚባለው ስንዴ ማምረት ጀምረናል በኛ አባቶች ጊዜ ግን ስንዴ አልነበረም፡፡
ጥ. በደርግ ጊዜ ጨርሶ አልነበረም?
መ. ነበር ግን እንደዚህ መሬት የሚይዝ ስንዴ አልነበረም፡፡ ዘርተንም የሚያዘረዝርበት ጊዜ አለ አሁን ተጠንቶ ስለመጣ በደንብ ነው ስንዴ የሚሆነው
ጥ. ስለበቆሎ እሳቸው ጀምረውልን ነበር መቼ እዚህ አገር እንደተጀመረና እንደተስፋፋ ቢገልፁልን?
መ. በፊት በብዛት በቆሎ ይዘራ ነበር አባቶቻችን ከብት ስለሚያረቡ ለከብቶች መኖም ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ለከብቶች መኖ በደንብ ሲያገኙ ሲጠቀሙ ወተት በብዛት ይገኛል፡፡ ወፍራም መሬት ስለሚፈልግ በብዛት ይመረት ነበር፡፡ አሁን ከብቶችም ስለሌሉ ወፍራም መሬትም ስለሌለ በቆሎ ማምረትን በስንዴ ተክተነዋል ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት የበቆሎ እርሻ በትንሹ ነው ያለው፡፡ በቆሎ በብዛት ባይመረትም አሠራሩን ቀይረን እየሠራን ነው በቆሎ ምርት ሊቀንስ የቻለው ከብት ስለሌለ ነው፡፡ በቆሎ በሳይንሳዊ መንገድ በኮምፖስ አዘጋጅተን ለመዝራት ደግሞ ሳናስብ የአየሩ ሁኔታ ችግር አለ፡፡ በቆሎ በአባቶቻችን ጊዜ መሬቱ ለምነው ከብቶቹም አሉ ማዳበሪያ በከብት ፍግ ተጠቅመን እንዘራለን ሼየ የሚባል ዘር አለ እሱ በ3 ወር ተኩል ይደርሳል፡፡ ካቱካና የምትባለው በ2 ወር የምትደርስ ግብርና አምጥቶ የምንጠቀምበት ነው አሁን ከብት ስለሌለ በኮምፖስ ተጠቀሙ ተብለን መንግስት ባደረገልን ምርምር እየተጠቀምን ነው ድሮ በአባቶቻችን ጊዜ የነበረው ዘር ሚያዝያ ይዘራል ዝናብ የሚችልም ነው የድሮውና የአሁኑ የተለያየ ነው ዘሩም አየሩም ተቀያይሯል፡፡ ሽዬ የሚባለው የበቆሎ ዘር ከሀረርጌ የመጣ ነው የመጣው አሁን የዝናቡ ሁኔታ እየቀነሰ ለሱ አልተስማማው ስለዚህ አሁን ካስማና ዘር ነው የምንጠቀመው፡፡ በቆሎ በቴክኖሎጂ ሄደንበት በይበልጥ ለማስፋፋት የውሃ እጥረት አለ ስለዚህ ውሃ ለማቆር ኘላስቲክ ያልፈልገናል ኘላስቲኩም በተደጋጋሚ ጠይቀን ልናገኝ አልቻልንም እናንተ የምትረዱን ቢሆን ተደራጅተንም ቢሆን፡፡
ጥ. የበቆሎ ዘር ከሀረርጌ እንዴትና ማን እንዳመጣው ቢገልፁልን? በጣሊያ ጊዜ ጣሊያኖች ባደረጉት ጥናት ላይ የዚህ አካባቢ ሰው ከብት ማርባት እንጂ እርሻ አያርሱም ብለዋል? ይሄ ትክክል ነው?
መ. ዘሩን ከሀረርጌ ያመጡት ሰዎች ናቸው በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመን ነው ጣሊያኖች ያሉት እውነት ነው ከብት ነበር ያለው እንዲያውም ዝሆንና አንበሳም ነበር ብለዋል፡፡ ጫካ ስለሆነ በዚያን ጊዜ አባቶቻችን እንደነገሩን ጣሊያኖች የፃፉት ትክክል ነው፡፡ በዛን ወቅት ብዙ ከብቶች ነበሩ በጣም ጫካ ስለሆነም አጥርም አያስፈልግም መውጫ የሚሆነውን ብቻ ዘግተን ነው እንጂ አጥርም የለ በዛን ወቅት ባንዳዎች ነበሩ እነርሱ ከብት ይዘርፉ ስለነበር እንዳይነኩ መውጫውን በሾክ ዘግተን ጫካ ውስጥ ነበር የምናሳድረው ይላሉ፡፡
ጥ. ስንት ከብት ነበራቸው አባትዎ?
መ. ከ7ዐ-8ዐ ነበረ የአንድ አካባቢ ሰዎች አብረን ነበር የምንጠብቀውም በቆሎ የሚዘራውም ለከብቶች ሲባል ነበር
ጥ. ጫካው ምን ዓይነት ዛፍ ነበር በብዛት ያለው?
መ. ግራር
ጥ. እርስዎ ስንት ከብት አለዎት?
መ. 3ዐ ይሆናሉ
ጥ. አሁን ደግሞ ስለሰዎች እናውራ እዚህ ያሉት ኦሮሞዎች የምን ጎሳ ናቸው ታውቃላችሁ አኗኗሯቸውስ?
መ. አደራ በቹ፣ ጉኢ፣ ቂምቢቺ የሚባል ብዙ ጎሳ አለ ባጠቃላይ ግን ኦሮሞ ነው የሚባለው እሚመራውም በሽማግልና ነው የጠፋም የሚቀጣው በሽምግልና ነው አሁንም በአንድ ሰፈር ሰባት አምስት ሆነን ተመካክረን ነው የምንሰራው፡፡
ጥ. የጎሳም ስም ማነው ደብረዘይት አካባቢ ያሉት አዳ ነን ብለዋል የዚህ ማን ነው የሚባለው?
መ. አመጣጣችን ከቢሸፍቱ አድአ ነው ይሄ አካባቢ ጫካና አንበሳ ነበረበት ቦታ ለመያዝ ጫካውን እያስፋፋን ነው የሚመጣውን ማንኛውንም ሰው ጎሳ አድርጎ እየያዘ ያለ ከቢሸፍቱ የመጣና በዚህ ኡሁ በወዲያ አድና ከፊንፊኔ ጀምሮ እስከ ወባ አሎጋ ድረስ
ጥ. ጊዜው ይታወቃል ወደእዚህ የመጡበት?
መ. ከታሪኩ እንደተረዳነው በጣሊያን ጊዜ ይመስለኛል
ጥ. ሉሜ ከየት ነው የመጣው?
መ. ሉሜ ማለት አመጣጡ ከግለሰብ ነው ሉሜ ሜቻ የሚባሉ ታዋቂ ሰው ነበሩ እኛ ሰውዬ ታዋቂ ባላባት ናቸው ሉሜ ሜቻ ይባላሉ እስከ አባቱ ኡሁ ከሚባል ጎሳ ነው የመጡት በእሳቸው ስም ነው ሉሜ ተብሎ የተጠራው
ጥ. ሉሜ ሜቻ በየትኛው ዘመን ወይም ማነው ባላባት አድርጎ የሾማቸው መቼ ነው በህይወት የነበሩት?
መ. ትክክለኛዉ ጊዜ አይታወቅም
ጥ. ቱኬ ማማን ታውቃላችሁ?
መ. ቱኬ ማማ የአርሲ ባላባት ነበሩ
ጥ. እዚህ አካባቢ የሚበቅለው ምን ምን ነው ጥራጥሬው?
መ. በእኛ አካባቢ ገብስ ባቄላ አተር ምስርና ሽምብራ ይሆናል /ይዘራል/
ጥ. እዚህ በብዛት ገበሬው የሚያመርተው ምንድን ነው? የግብርና ባለሙያ እንደመሆንዎ?
መ. ባቄላና አተር
ጥ. እዚህ አካባቢ ሽንኩርት የለም?
መ. በመስኖ ይጠቀማሉ
ጥ. የጠፋ የተተወ ሰብል አለ በፊት የነበረ አሁን የጠፋ?
መ. አለ፡፡ ዘንጋዳ በፊት ነበር አሁን ጠፍቷል ድሮ በመጋቢት ተዘርቶ 5 ወር ይፈጅበታል፡፡ ሀብታም የሚባለው የሚዘራው በዛን ዘመን ዘንጋዳ ነበር፡፡ አሁን አየሩ አልተስማማውም ጠፋ
ጥ. ስለ አየር ንብረት የምታውቁት የሙቀት መጠን የዝናብ ሁኔታ አንድ ዓይነት ነው ከበፊቱ ጋር ወይስ ተቀያይሯል?
መ. አዎ ተቀያይሯል፡፡ ድሮ ቆላ ቢባልም እንደዚህ አይሞቅም ዝናቡም አሁን ወቅቱን ጠብቆ አይመጣም እንዳለ ነው የተቀያየረው ባለፈው ጥቅምት ዝናብ ጥሎ ነበር ቅዝቃዜው በጣም ሀይለኛ ነበር የደጋ እዚህ እንደዚህ አይቀዘቅዝም ነበር፡፡ ቆላም ቢሆን ለሊት ልብስ ለብሰን ነው የምናድረው አሁን ግን ልብስ ለብሶ የሚተኛ የለም ስለዚህ በአጠቃላይ ተቀያይሯል፡፡
ጥ. አፈሩ ለምነቱ ተቀይሯል?
መ. አዎ አፈሩ ለምነቱን አጥቷል የኛ ሀገር መሬት ወፍራም ነው አባቶቻችን መሬቱን ቀያይረው ነበር የሚዘሩበት መሬት ትርፍ ስለሆነ ችግር አልነበረም አሁን እሱ ጠፋ እንዲያውም ማዳበሪያ ለምነቱን አጠፋብን ብለን ማሰብ ጀምረናል፡፡
ጥ. አሁን ያለማዳበሪያ አትዘሩም?
መ. ጤፍ ያለማዳበሪያ ፈጽሞ እየዘራም ድሮ ያለማዳበሪያ ነበር የሚዘራው፡፡ እንዲያውም ግብርና ሚ/ር የአየር ሁኔታው ጋር የሚስማማ ምርጥ ዘር እያመጣልን ነው እንጃ በጣም ችግር ነው፡፡
ጥ. አንድ ሰው መጥቶ ገበሬው ካሉበት ችግሮች መካከል አንዱን ልፈታላችሁ እችላለሁ የምፈታው ግን አንድ ብቻ ነው ቢል ዋና ችግራችን ብላችሁ የምትመርጡት ምንድነው?
መ. የአየር ሁኔታው ችግር ስለሆነ ኩሬ ማዘጋጀት አለብን ይህን ለማዘጋጀት ላስቲክ /ጀሪካል/ ያስፈልጋል ይህንን የሚረዳን ብናገኝ፤ የማዳበሪያ ችግር የማዳበሪያ ዋጋ መጨመርም ትልቁ ችግራችን ስለሆነ እነዚህን እንደ አንድ ችግር ቢያዙልን፡፡
ጊዜያችሁን መስዋዕት በማድረግ ለሰጣችሁን ማብራሪያ በጣም አመሰግናለሁ፡፡
1

Transcript: Download (191 KB)
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Debele, Bete
Dabi, Alamu
Bekele, Getnet
Dabi, Alamu
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
- Farmers’ testimonies on the history of agriculture and environmental change
- The state of the area’s agriculture in the contemporary period (after 1991)
- Cropping patterns and the reasons behind them
- Interview conducted in Ejersa Gerro, Lume, Lake region, Ethiopia
Date: June 7, 2010
Location: Ejersa Gerro, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
Oromo
Oromo
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University