Ethiopian Farmers >
Interviews >
Kase Gosa, Ejegu Sheberu, Denberu Mamo, Demesew Tulula, and Tadese Alemu Interview

Audio File:
Download File: Download
Download File: Download
Transcript:
Open/Close
እኔ ፕሮፌሰር ጌትነት በቀለ እባላለሁ፡፡ የመጣሁት ከአሜሪካን ሀገር ነው ዓለም ባንክ ኦክላንድና ሚሽጋን ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመሆን አንድ ጥናት ለማድረግ ነው የጥናታችን ዋና ዓላማ ስለ የአየር ሁኔታ (Enviroment) ያለበትን ሁኔታ ለማጥናት ሲሆን በተለያየ ሳይንሳዊ መንገድ የሚደረገው ጥናት የአካባቢውን ነዋሪዎች /ገበሬዎች/ ያካተተ ባለመሆኑ ብዙም መፍትሔ ስላላመጣ የአካባቢው ነዋሪዎች የገበሬዎቹ ሃሳብ የሚፈልጉት ምንድነው የሚለውን ይዘን በተለያየ ቦታ ጥናት እያደረግን ነው የጥናታችንም ዋና ዓላማ አካባቢያችን እንዴት ነው የምናሻሽለው ዝናቡ ለምንድነው የሚጠፋው መሬቱ ምን እየሆነ ነው እንዴት ተለወጠ የሚለው ላይ ለመነጋገር ነው በተለይ የድሮውን የምታውቁትን እስከምታውቁት ድረስ የሰማችሁትንም ቢሆን እንድትገልፁልኝ እፈልጋለሁ፡፡
እራሳችሁን ካስተዋወቃችሁኝ በኋላ ቀጥታ ወደ ጥያቄና መልስ እንገባለን፡፡
1. አቶ ጎሣ ካሣዬ እባላለሁ የተወለድኩት እዚሁ ቀበሌ ውስጥ ነው በግብርና ነው ቱሉ ወረዳ ነው፡፡
2. አቶ ታፈረ ጎዴ አባላለሁ ትውልዴ እዚሁ ነው የምትዳደረውም በግብርና ነው
3. አቶ እጅጉ ሽብሩ አባላለሁ ዕድሜ 53 እዚሁ ተወልጄ እዚሁ ነው የምሰራው
4. አቶ ድንበሩ ማሞ ዕድሜ 43 ስራ ግብርና
5. አቶ አበበ ዝናብ እዚሁ ተወልጄ ዕድሜ 32 ተማሪ ነበርኩ አሁን የምተዳደረው በግብርና ነው
6. አቶ ደምሳቸው ግርማይ ትውልዴ እዚሁ ነው ዕድሜ 33 በ1987 ትምህርቴን ጨርሼ ነው ወደ ግብርና የገባሁት የህብረት ሥራ ማህበር የሂሳብ ሥራ እሠራለሁ፡፡
7. ወ/ሮ ህይወት ሀይሌ የግብርና ባለሙያ ነኝ ግብርናን ወክዬ ነው እዚህ የተገኘሁት
ጥ. ሁላችሁም እዚህ ያላችሁት የምታርሱበት የራሳችሁ የሆነ መሬት አላችሁ?
መ. የሌለንም አለን በኮንትራት እንሠራለን
ጥ. የሌላችሁ ሰዎች ለምን መሬት እንደሌላችሁ ብታስረዱኝ
መ. እኔ መሬት በሚሰጥበት ጊዜ አልደረስኩም አልተወለድኩም አባቴ ከራሱ መሬት ላይ አንድ ቀርጥ መሬት ሰጥቶኝ በሱ ነው የምተዳደረው በተጨማሪም እየገዛሁኝ ነው የማርሰው
ጥ. እየገዛሁ ስትል እንዴት ነው?
ጥ. በኮንትራት እየያዝኩኝ ማለቴ ነው
ጥ. ገበሬ ማህበር መሬት አይሰጥም እንዴ?
መ. መሬት የለም ስለዚህ አይሰጥም
ጥ. ሌላ መሬት የሌለው አለ ማን ነው?
መ. መሬት የሌለን ወጣቶቹ ነን
ጥ. ወጣቶቱ መሬት ከሌላቸው ወደፊት ምን የሚሻል ይመስላችኋል? ለወጣቶቹ ምን ተስፋ አላቸው ሌላ ስራ መፈለግ ነው ያለባቸው ወይንስ ምን እስኪ እዚህ ላይ አስተያየታችሁን ብትሰጡኝ?
መ. ወደፊት መሬት የማግኘቱ ሁኔታ ተስፋ የለውም በህብረት ተደራጅተው አንዳንድ ሥራዎችን መስራት እንጂ መሬት ከእንግዲህ ወዲያ እየጠበበ እንጂ ስለማይሰፋ ከብት እርባታ ዶሮ እርባታ የመሳሰሉትን ስራዎች ነው መስራት ያለባቸው
ጥ. ሌላ ተጨማሪ አስተያየት ያለው ካለ በዚህ ሃሳብ ላይ?
መ. በአሸዋ ላይ ለምሳሌ በወንዝ አካባቢ ወጣቱ ተደራጅቶ በአሁኑ ሰዓት አሸዋ በማምረት እየሠሩ አሉ ይህንን መስራት ይችላሉ እንዲሁም የድንጋይ ካባ ባለበት አካባቢ በመደራጀት ማውጣት ይችላሉ፣ እንዲሁም ዶሮ እርባታ የመሳሰለውን ሥራ መንግስትም ድጎማ እያደረገ ስለሆነ በዚህ መልኩ መተዳደር ይችላሉ፡፡
ጥ. እንግዲህ አሁን ለወጣቶቹ ከእርሻ ሥራ ይልቅ ተስፋቸው በሌላ ሥራ መስክ ነው ማለት ነው?
መ. አዎ ትልቁ ነገር መሬት ከደርግ ጊዜ ጀምሮ የተለካበት ነገር የለም ያለው እዛው በነበረበት ሥርዓት ነው የእርሻ መሬትም ያለው ጠባብ ነው አንድ ገበሬ ያለው ቢበዛ ከአንድ ሄክታር እስከ ሶስት ሄክታር ብቻ ነው
ጥ. ከሶስት ሄክታር በላይ ያለው የለም?
መ. የለም ስለዚህ አባት ለልጁ ካለው ሶስት ሄክታር ላይ አንድ ቀርጥ ይቆርጥለታል ያችን በማባዛትና ከሌላው ኮንትራት በመያዝ ይጠቀማል /ይተዳደራል/ ምንም ከሌለው ደግሞ ያው ቅድም እንደተገለፀው በመደራጀት ነው የሚሰሩት መንግስትም ሁኔታውን ያመቻቻል፡፡
ጥ. አንድ ቀርጥ ማለት ስንት ነው?
መ. ሃምሳ ሜትር በሃምሳ ነው
ጥ. ስለመሬት መከፋፈል አንስታችሁ ነበርና እስሲ ስለሱ ትንሽ እንነጋገርበት በደርግ ጊዜ ነው መሬት መከፋፈል የተጀመረውና ከዛ በፊት ስላለው እንነጋገራለን ደርግ በገበሬ ማህበር መሬት ማከፋፈሉ ጥሩ ነው ትላላችሁ? ወይስ ጥሩ አይደለም? ከዚህ የተሻለ አማራጭም ካለ ሃሳባችሁን ስጡ?
መ. ደርግ ሳይመጣ ትንሽ ሰዎች ነበሩ መሬት ይዘው ቁጭ ብለው የነበሩት በዛን ጊዜ ሌላው ጭሰኛና ተበዳይ ነበር ደርግ ሲመጣ መሬት ለሁሉም ሰጠ ሁሉም ባለ መሬት ሆነ ምርትም ከዛ ወዲህ ነው ማምረት የተጀመረው የሌለውም በአሸዋ እየተደራጀና መሬት እየተኮናተረ ይሠራ ነበር ደርግ ባይመጣ ኖሮ ትንሽ ሰው ነበር መሬት ይዞ የነበረው ለቀበሉ ብቻ ነበር ሠርቶ የሚኖረው
ጥ. ትንሽ ሰው ነበር መሬት የያዘው ብለውኛል እነሱ እነማን ናቸው?
መ. በአሁኑ ሰዓት እነሱ የሉም ሁሉም አልፈዋል
ጥ. ሌላው ገበሬ እንደጢሰኛ ሆኖ ነበር የሚያገለግለው ማለት ነው አንዳንዶቹን በህይወት ባይኖሩም ስማቸውን አታስታውሱም?
መ. መምሬ ደስታ የፀሐፊ ትዕዛዝ መሬት የመልከኛ ይባላል፡፡
ጥ. መልከኛ የሚባሉት እነማን ናቸው?
መ. መልከኛ የሚባሉት እዚህ አካባቢ ተሊላ በዳዳ የሚባሉ ነበሩ
ጥ. ብዙ መሬት ነበራቸው?
መ. አዎ ብዙ መሬት ነበራቸው አንድ ሰው ነው ይዞ የነበረው
ጥ. በደርግ ጊዜ አንድ ሰው ይዞት የነበረውን ነው የተከፋፈለው?
መ. አዎ አንድ ሰው ይዞት የነበረውን ብዙ ሰው ይጠቀምበታል ማለት ነው
ጥ. ከደርግ በፊት ስላለው ሁኔታ የምታውቁት አላችሁ? በእርግጥ አንዳንዶቹ ትንንሾች ናችሁ ለምሳሌ የባላባት መሬት የሚባል ነበር?
መ. ባላባቶች የሉም
ጥ. በእርሻው የምትዘሩት አዝርዕት አይነት ምን ያህል ተቀያይሯል? ወይስ አንድ ዓይነት ነው የምትዘሩት አሁንስ በብዛት ምንድነው የምታመርቱት?
መ. አሁን ምርጥ ዘር ነው የምንዘራው ድሮ ያራንዳቶ የሚባል ስንዴ ነበር የምንዘራው እሱ ጠፍቷል ጨርሶ የለም አሁን ምርጥ ዘር ነው የምንዘራው
ጥ. ድሮ የሚሉት መቼ ነው በደርግ ነው?
መ. በአፄ ኃ/ስላሴ ጊዜ ነው በዛን ጊዜ ያራዳቶ ስንዴንና ትንሽ ጤፍ ነው የምንዘራው
ጥ. በብዛት ሰንዴ ነበር የምትዘሩት?
መ. አዎ በብዛት የምንዘራው ያራንዳቶ የሚባለውን ስንዴ ነበር ጤፍ በትንሽ እንዘራ ነበር ማዳበሪያ በዛን ጊዜ አልነበረም ማዳበሪያ መግባት የጀመረው ቆይቶ ነው አሁን ግን ምርጥ ዘር ነው የምንዘራው
ጥ. ምርጥ ዘሩ የስንዴ ብቻ ነው? ጤፍና ሌሎቹስ?
መ. የጤፍ የለም ስንዴ፣ ሽንብራ፣ ነው የምናገኘው ጤፍ ዘንድሮ ይጀምራል ተብሏል፡፡
ጥ. ቅድም መሬት አንሶናል እየተኮናተርን ነው እምናርሰው ያሉ ሰዎችን አናግሬ ነበር መሬት አንዴት አገኛችሁ ከቤተሰብ ነው? ወይንስ ከገበሬ ማህበር ይህንን ብትገልፁልኝ? አሁን አንተ ወጣት ነህ እንዴት አገኘህ?
መ. እኔ ያው ቅድም እነሱ እንደተናገሩት በደርግ ጊዜ ልጅ ነበርኩኝ ቤተሰቤም ደካማ ነበሩ በደርግ ወቅት የዘማች እርሻ አለ የህብረት እርሻ አለ በቤተሰብ ስር እኔ ተወክዬ ማህበር ብገባ ቤተሰብ የሚልከው ሰው የለም ግድ የቤተሰብ መሬት ይወሰዳል በማህበርና በዘማች እርሻ ካለተሳተፉ መንግስት መሬት ይወስዳል ገበሬ ማህበር ለመግባት ዕድሉን አላገኘሁም ተልኬና ጦሬ ነው የቤተሰብ መሬት የያዝኩት
ጥ. ሌሎችስ እንዴት እንዳገኛችሁ ብትገልፁልኝ?
መ. አሁን መሬት በዛን ጊዜ 18 ዓመት ከሞላ እናትና አባት መሙላቱን አረጋግጠው ነው መሬት የሚሰጠን የሚሰጠው መሬት ሁለት ቀርጥ ተኩል ነው ከዛ በላይ የለም ከዛ ደግሞ አንድ ቤተሰብ ካለኝ ተኩል ይጨመራል እኔ እንደዚህ ነው ያገኘሁት
ጥ. እርስዎ የማን መሬት ተሰጠዎት?
መ. የመንግስት መሬት ነው የተሰጠኝ አባቶቻችን የላቸውም እኛ የሰው ነበር የምናርሰው
ጥ. እርስዎ ያን ጊዜ የተሰጠዎት መሬት ከዛ በፊት ያልታረሰ መሬት ነው ወይንስ ሌላ ሰው ያረሰው
መ. ያልታረሰም አለ የታረሰም አለ?
ጥ. ስለ ድሮ ብጠይቃችሁ ታውቃላችሁ ለምሳሌ በአፄ ምኒልክ ዘመን እንዴት አንደነበር የሰማችሁት ካለ ስለ አስተራረሳቸው?
መ. እኛ የሰማነው ታሪክ የለም
ጥ. አንዳንድ መረጃዎች በድሮ ጊዜ በዚህ አካባቢ የከብት አርባታ በጣም የተስፋፋ እንደነበርና የእርሻ ስራ ከመስራት ይልቅ ገበሬዎቹ ከብት ማርባት ይፈልጉ እንደነበር ይባላል ይህን የሚያው አለ?
መ. ይሄ ትክክል ነው እኔም በእረኝነትም ቢሆን ትንሽ ደርሼበታለሁ፡፡ ያኔ የነበረው ከብት ብዛት በጣም ብዙ ነበር በጥራትም አሁን ካለው ጋር በምንም አይገናኝም ያኔ በጣም ጥሩ ምኩቱ ነበር ያለው አሁን ግን ከብቱ እራሱ ማገዶ ነው፡፡
ጥ. ይሄ ችግር ታዲያ ከምን የመጣ ይመስላችኋል?
መ. አሁን ቤተሰባችን ሰፊ ነው እነሱን ለማስተዳደር ለማገዶ ደን እየተጨፈጨፈ እርሻ እየበዛ የግጦሽ መሬት እየጠፋ ነው የመጣው
ጥ. የግጦሽ መሬቱ እየታረሰ ከሄደ ያለው አማራጭ ከብት መቀነስ ነው ማለት ነው?
መ. አዎ በዚህ ምከንያት ነው አማራጭ የለም
ጥ. እርስዎ ደርሰውበታል በትክክል ከብት በነበረበት ጊዜ
መ. አዎ በትክክል ደርሼበታለሁ እረኝ ነኝ በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመን ነው አሁን የተገለፀው ሁሉ ትክክል ነው የድሮና የአሁን ከብት ምንም አይገናኝም ድሮ አንድ ወይፈን ሲወለድ በ3 ዓመት ነው የሚያርሰው ዛሬ ግን በ1ዐ ዓመት አያርስም የሚበላ ነገር የለም መሬት የለም ሁሉም ቤተሰብ አለው ከብት የሚበላው ያችኑ ያረሳትን ገለባ ብቻ ነው እንጂ ሣር የለም የድሮ ከብት ሣር ይበላል፡፡ የድሮ ፍየል ቅጠል አለ ቅጠል ይበላል፡፡
ጥ. በአፄ ኃ/ስላሴ ጊዜ መሬት በጥቂት ባለሀብቶች እጅ የተያዘ ነበር ብላችኋል፡፡ እነርሱ እንግዲህ የዛን ጊዜ የራሳቸውን ጭሰኛ አምጥተው ነበር የሚያሳርሱት ይባላል በዛን ወቅት የሰው ጉልበት ባለመገኘቱ ይሆን እርሻውን ትተው ወደ ከብት እርባት የገቡት?
መ. በዛን ወቅት ሰው ለእነሱ ግብርና ነው የሚያገለግለው ደርግ መሬት ካከፋፈለው በኋላ ነው ለራሱ የሠራው
ጥ. ጭሰኞች ግብር የሚገብሩት ምን ያህል ነበር?
መ. እኩል የሚያርሱ ሲሶም የሚያርሱ አሉ እንደዚህ ነበር
ጥ. በጣሊያን ዘመን እዚህ አካባቢ ጣሊያኖች ያደረጉት ነገር አለ? ሌላ አካባቢ ሳነጋግር ደብረዘይት አካባቢ በጣሊያን ጊዜ /ዘመን/ እርሻ ሁሉ በእነርሱ ምክንያት ነው የተስፋፋው ብለዋል የምታውቁት አለ ?
መ. ምንም የምናውቀው የለም አብዛኞቻችን ልጆች ነን፡፡ መንገድና ድልድይ ሰሩ ሲባል እንጂ እርሻ አረሱ የሚለውን አልሰማንም
ጥ. ለምንድነው የምታርሱት?
መ. ለምንበላው ነው
ጥ. መጀመሪያ እርስዎ ወደ እርሻ ሲሄዱ የምበላውን ልረስ ብለው ነው የሚሄዱት?
መ. ሌሊት ስተኛ አስባለሁ ቀለብ ምን እንደሚሆን ልጆቼን አስባለሁ ይሄ መሬት መገልበጥ አለበት ብዬ ማወቅ አለብኝ ያን ካረኩ በኋላ ወደ እርሻ እገባለሁ፡፡
ጥ. በመጀመሪያ እርስዎ እርሻ ሲያርሱ የሚያስቡት ቤተሰቤን ምን አበላለሁ የሚለውን ነው
መ. አዎ እሱን ነው የማስበው
ጥ. አርሼ ሸጨ ገበያ ሞጆ፣ አዲስ አበባ ይሄ ይፈለጋል የሚለውን አስበው አያውቁም?
መ. ይሄንን የማስበው በሁለተኛ ደረጃ ነው ዋናው የምናመርተው ለቤተሰብ ነው መጀመሪያ ራሳችንን አድነን ነው ወደ ገበያ የምናስበው ዛሬ የማርሰው ለቀለብ ለቤተሰብ ልብስ ለትምህርት ቤት የሚለውን እናስባለን በተራ
ጥ. እዚህ አካባቢ አብዛኞቻችሁ የምትመገቡት ምንድነው ለምሳሌ አሁን ምሳ ምን ትበላላችሁ?
መ. እንጀራ በሽሮ
ጥ. ይሄ ምግባችሁ ከቤት ያመረታችሁት እንጂ ገዝታችሁ አይደለም?
መ. አዎ አንገዛም ከቤት የተመረተ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የምንገዛው ይኖራል ዘንድሮ ግን አምርተን ለማዳበሪያ ዕዳ ለመክፈል ነው የተዘጋጀነው ለቀለብ ከብትም ቢሆን እንሸጣለን፡፡
ጥ. ከምታመርቱት ምርት ምን ያህሉን በዓመት የምትሸጡ ይመስላችኋል?
መ. ብዙ ነው የምንሸጠው
ጥ. በግምት 1ዐ ኩንታል አንድ ገበሬ ቢያመርት ምን ያህሉን ይሸጣል
መ. የማዳበሪያ ዕዳ ካለበት ሙሉውን ሽጦ ይከፍልና ከብት ሸጦ ቀለብ ይገዛል
ጥ. ከገበያ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ከፍ ያለ ነው ማለት ነው?
መ. አዎ ለምሳሌ የተወሰነውን ለራሳችን የተወሰነውን ለገበያ እናደርጋለን
ጥ. ብዙ ጊዜ የት ነው የምትሸጡት?
መ. ሞጆ ወስደን ከተማ ነው የምንሸጠው
ጥ. እዚህ ድረስ መጥቶ የሚገዛችሁ ነጋዴ የለም ?
መ. የለም አንዳንድ ጊዜ አገልግሎት ይገዛል እሱ ወዲያው ገንዘብ አጥቶ ይቆማል ስለዚህ ገበያ ወስደን ተንገላተን ነው የምንሸጠው
ጥ. በምንድነው የምታጓጉዙት እህሉን?
መ. በአህያ
ጥ. አንዳንዶቻችሁ በአሁኑ ወቅት የገበሬው ችግር ምንድነው ዋና የምትሉትን አንድ ንገሩኝ ሶስት አራት ሳይሆን ብትባሉ ምንድነው የምርመርጡት
መ. ዋና ችግራችን ማዳበሪያ ነው በፊት የሚሰጠን በብድር መልክ ነበር አሁን ግን ገዝተን ነው የምንጠቀም በብድርም ብንወስድ ከብት ሸጠን የታረሰ መሬት ሸጠን ነው የምንከፍለው አሁን የምናመርተው ምርትም ጥራጥሬ ነው ጤፍ መዝራት አይቻልም የሚዘራባቸው የተወሰኑ ናቸው ማዳበሪያ የማይፈልጉ ቦሎቄ፣ ባቄላ አተር ነው ዋናው ችግራችን ማዳበሪያ ነው፡፡
ጥ. የማዳበሪያ ዋጋ ከፍተኛ መሆን ነው ወይንስ ማጣት?
መ. ዋናው ዋጋው መናሩ ነው አብላጫው በኛ ማዕከል ያሉት ወጣቶች ናቸው ስለዚህ መሬት የላቸውም የሚሠሩት ተከራይተው ነው ለመሬት ያወጣሉ፣ የማዳበሪያ ዋጋ በመናሩ ምክንያት የተኮናተሩትን መሬት መለሰው ይሸጣሉ፡፡
ጥ. ሁላችሁም በዚህ ሃሳብ ትስማማላችሁ?
መ. አዎ ልክ ነው እንስማማለን ቀደም ሲል ማዳበሪያ ልምድ ነበረው በአንድ ጊዜ ትተህ ውጣ ሲባል ሁሉም ገበሬ ነው የተቸገረው እንኳንስ ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ ገዝቶ ሊዘራ ቀርቶ ከቤቱ አንድ ቡናና 5 ኪሎ እህል ይዞ የማይወጣ ገበሬ አለ ቀደም ሲል ምርጥ ዘር በብድር ነበር አሁን እነሱ ሁሉ ቀሩ አሁን የስንዴ ምርጥ ዘር መጥቶ ነበር ግን ለመውሰድ ፈቃደኛ ብንሆንም በምን አቅሙ ይውሰድ ገበሬው ማዳበሪያ ግዢ ምርጥ ዘር ግዢ ሲሆን ገበሬው የሚገዛበት አቅም የለውም
ጥ. ማዳበሪያ በብድር ትወስደላችሁ?
መ. በፊት እንወስድ ነበር አሁን ሙሉ በሙሉ ግዢ ነው
ጥ. መቼ ነው እዚህ አካባቢ በብዛት ማዳበሪያ መጠቀም የጀመራችሁት?
መ. የጀመርነው በአፄ ኃ/ስላሴ ነው በደንብ ግን መጠቀም የተጀመረው በ1969 ነው፡፡ በማህበር እየተደረገ ነው የተጀመረው
ጥ. ለምን ማዳበሪያ ትጠቀማላችሁ የድሮ ገበሬዎች አይጠቀሙም ለምን ይመስላችኋል?
መ. ያኔ ህዝቡ ትንሽ ነበር አሁን ህዝብ ጨምሯል በፊት በ6 ሰው የተያዘው ጋሻ አሁን ያ መሬት 8ዐ ሰው ነው የያዘው ያኔ መሬቱ ብዙም አልታረሰም ስለዚህ መሬቱ ማዳበሪያ አላስፈለገውም አሁን ግን ህዝብ ስለበዛ ሁሉም ተመንጥሮ ስለታረሰ ለምነቱን ስላጣ ነው ማዳበሪያ ያስፈለገው፡፡ በፊት ጓያ ሽምብራ ነበር የሚዘራው አሁን የሚዘራው ጤፍ ነው፡፡
ጥ. ከሌላው ጊዜ በበለጠ ለምን ነው አሁን ጤፍ የሚዘራው?
መ. ጤፍ የሚዘራው ገቢ ስለሚገኝበት ነው ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማሟላት የሚቻለው ጤፍ ተሽጦ ነው ጤፍ ዛሬ አንድ ሺ ብር ሲሆን ስንዴ 4ዐዐ ወይም 45ዐ ነው ይህንን ሸጠህ ማሟላት የምትፈልገውን ማሟላት አትችልም ጤፍ ከሸጥክ ግን ትቋቋመዋለህ፡፡
ጥ. የአየር ንብረት መዛባት እየተፈጠረ ነው ይባላል እናንተ ያስተዋላችሁት ነገሮች አሉ የዝናብ መዛባት የመሞቅ ወይም የመቀዝቀዝ ነገር ልብ ያላችሁት አለ?
መ. አዎ የዛሬ 7 ዓመት ቀደም ቀደም አድርገን ዘራን ዝናቡ ወዲያው በአበባ አቋረጠ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጤዛ ይጥልና ከጣለ በኋላ ቀይ ነገር አለ ዋግ ይጥላል ማለት ነው፡፡ የአየር ሁኔታው በጣም ጥሩ አይደለም እየፈራን ነው ለጥራጥሬ ነው እንጂ ጤፍ ቢዘራ ይውጠዋል፡፡ የሚጥለውም ዝናብ አጥጋቢ አይደለም በዚሁ ከዘለቀ በተለይ ለጤፍ አይመችም በጣም ያሰጋል፡፡
ጥ. ቅድም ስጠይቅ ዋናው ችግራችን ማዳበሪ ነው ብላችሁ ነበር በበሽታስ በኩል የሰው፣ የከብትም ሆነ አዝርዕትም ላይ የመጣ በሽታ ወይም እንደወረርሽኝ ያለ ነገር ተምች ሊሆን ይችላል የተከሰተበት ጊዜ አለ በእናንተ ዘመን?
መ. እዚህ አካባቢ ባጋጣሚ ወቅቱ ትዝ አይለኝም እንጂ ጤፍ ዘርቼ ተምች እንዳለ ወሮት መድሀኒትም ቢረጭ ወደ ሌላ እየተሳበ አበላሽቷል፡፡ ከዛ ወዲህ ግን አላጋጠመኝም፡፡ ጤፍ ዝርዝር ላይ ህዳርና ታህሳስ አካባቢ ፌንጣ ይመጣል እሱ ብዙ ጊዜ ያጋጥማል፡፡
ተባይ ተለይቶን አያውቅም ሽምብራ፣ ምስር እና በተለይ አተር ላይ በጣም ያጠቃዋል መድሀኒት ከነጋዴዎች እየገዛን የልማት ሠራተኞችም እየተባበሩን መድሀኒት እየረጨን ነው እንጂ ተለይቶን አያውቅም ሽምብራና ጥራጥሬ ይዘራል እንጂ ብዙ ፍሬ አይገኝበትም፡፡
ጥ. መድሀኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ ታወጣላችሁ?
መ. አዎ በአመት አንድ ሰው እስከ ሁለት ሊትር ይገዛል አንዱ ሊትር 2ዐዐ ብር ሂሳብ ነው ስለዚህ ይወጣል፡፡
ጥ. ይሄ ከማዳበሪያ ወጪጋር ሲደመር ይበዛባችኋል ማለት ነው?
መ. አዎ ባለፈው ሽምብራ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ምስር ሲያብብ ስለሚቀረጥፈው የግድ መድሀኒት ያስፈልጋል መድሀኒቱን ከግል ነጋዴዎች እንገዛለን ጥሩ ነው ይላሉ ግን ጥቅም ሳይሰጥ ይቀራል እህሉንም ሊጎዳ ይችላል፡፡ ኪሳራ ያስከትላል፡፡
ጥ. በግብርና ሚኒስቴር በኩል እነዚህ መድሀኒቶች አይቀርቡም?
መ. ሙሉ በሙሉ አይገኝም አይቆጣጠሩትም ከዛ የምናገኘው ደግሞ ተባዩን አይፈጀውም ከግል የምንገዛው ይሻላል፡፡
ጥ. ስለ ደን ሁኔታው እንዴት ነው እዚህ አካባቢ ደን ድሮ ነበር? ወይንስ አሁን? ያለ በጠቅላላ ብታስረዱኝ
መ. ደን ድሮ ታች ታቹን በሙሉ ጫካ ነው መተላለፊያ አልነበረም የተለያየ አይነት በእኔ ዕድሜ አሁን ግን አንድ እንጨት አይታይም ድሮ አጥር ለማጠር ወጣ ብለን ቆርጠን መጥተን ነበር አሁን ግን ምንም የለም ያው የሚታይ ነው፡፡
ጥ. በዚህ ላይ ተጨማሪ ካለ
መ. ስለ ደን ጉዳይ ከተነሳ ህዝባችን በከብት ነበር የሚተዳደረው የሚለው ትክክል ነው ጤፍ ለምንድነው የሚዘራው የሚለው ለከብትም ምግብነት ጭምር ነው ከመሬት ጥበት የተነሳ ደኑ እየተመነጠረ ወደ እርሻ ተገብቷል የግዴታ ከዓመት ዓመት ተመንጥሮ ወደ እርሻ ተገብቷል፡፡ አሁን ለማገዶ እንኳን ሁሉም በደጁ ባህር ዛፍ እየተከለ ነው የሚጠቀመው
ጥ. ስለዚህ ከብቶችና ዛፎች በአንድ አካባቢ ነው የጠፉት ማለት ነው?
መ. አዎ
ጥ. እርሻ ሲጀመር እዚህ አካባቢ የከብት ፍግ ትጠቀሙ ነበር?
መ. አዎ ይደረግ ነበር ግን አሁን እንጨትም ስለጠፋ ሰው ኩበት አድርጎ ለማገዶ ሰለሚጠቀምበት ፍግ ብዙ አይገኝም፡፡ ገበሬ ኩምፖርስ መስራት አላወቀበትም እንጂ ከአጤፋሪስ ከአራሙቻ ኮምፖስ መስራት ይቻላል፡፡ ከብት የማነሱ ነገር እውነት ነው ግን ከቅጠልም ይሰራል ከምፖስ ግን ገበሬው ዕውቀት የለውም እኔ ይህንን ያወቅኩት ሰልጥኜ ነው፡፡
ጥ. ገበሬዎች ከከብት ፍግ ማዳበሪያ እንደሚገኝና የተሻለ ምርት እንደሚገኝ ያውቃሉ?
መ. አዎ ያውቃሉ ግን አይጠቀሙበትም አሁን እያንዳንዱ ቤት ብንሄድ ይገኛል ግን አይጠቀሙበትም
ጥ. መሬት አለን ያላችሁ ሰዎች መሬታችሁን መሸጥ መለወጥ እሱን አስይዞ ገንዘብ መበደር ትችላላችሁ?
መ. ማኮናተር እንችላለን መሸጥ ግን አንችልም
ጥ. መሬት መሸጥ ቢፈቀድ ጥሩ ይመስላችኋል? ወይስ መጥፎ?
መ. መሬት እንዴት ይሸጣል መሸጥ የለበትም
ጥ. ለምን?
መ. መሸጥ ቢቻል ለጊዜው ገንዘብ እናገኛለን ገንዘቡ ሲያልቅ ግን ተጎጂ እንሆናለን መሬቱም ከኔ አልፎ ቤተሰቤም ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ከተማ ጥሩ መሬት ነበራቸው ወደ መቶ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ግምት አገኙ አሁን ግን ምንም የላቸውም
ጥ. ሌላ ማጠቃለያ ሃሳብ አላችሁ?
መ. ቅድም ሲያቀርቡ አንድ ያላችሁን ችግር ንገሩኝና እፈታለሁ ብለዋል ምናልባት ያንን የማዳበሪያ ችግር መቅረፍ እንኳን ባይቻል ማዳበሪያ ስንጠይቅ ኮምፖስት ተጠቀሙ ነው የምንባለው እና ሌላም ውሃ ችግር አለና ያንን ውሃ እንኳን ወደዚህ ለማቅረብ የሚቻልበት መንገድ ቢመቻች፡፡ እኔ 8 ልጆች ቢኖሩኝ 8 ቀረድ ሊኖረኝ ይችላል እነሱ ከሰኔ 3ዐ እስከ መስከረም 2 ነው የሚኖሩት አረም የሚመጣው ከዛ በኋላ ነው እነርሱ ት/ቤት ይገባሉ መንግስት የተዘራው መሬት እንዳይበላሽ መድሀኒት አዘጋጅቷል ይህንን ባልና ሚስት አርሞ ስለማይቻል ማዳበሪያ ቢመጣልን ይህንን ለማለት ነው፡፡
የማዳበሪያ ችግር የዚህ ሀገር ችግር ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ያለ ችግር ነው ህንድ ለምሳሌ እንውሰድ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ናት አብዛኛውም ህዝብ በግብርና የሚተዳደር ሲሆን ማዳበሪያ መጠቀም ከዛ ነው የተጀመረው እና አሁን የማዳበሪያ ዋጋ መጨመር እያሳሰበ የመጣ ነገር ነው ማዳበሪያን የሚያቀርበው የዓለም ባንክ ነው የዓለም ባንክ ደግሞ አሁን እንዴት ልረዳ እችላለሁ እያለ እያሰበ ነው ይህም ጥናት ያስፈለገው፡፡
ችግራችሁን ለማወቅና የመፍትሔ ሃሳብ ለማምጣት ነው ስለዚህ ይህ የደረግነው ውይይት ይጠቅመናል ምን መደረግ አለበት የሚለውን ያመላክታል፡፡ እናንተ አሁን ማዳበሪያን እየፈለጋችሁ ነው አንዳንድ አካባቢ ደግሞ ይህንን ማደበሪያ አስቀሩልን መሬታችን ጉቦ ለመደ ያሉ አሉ፡፡ ከእናንተ ግን ጠቅሞናል ትላላችሁ ስለዚህ በነዚህ ሃሳቦች ተነስተን ጠቃሚ ስራ እንሠራለን፡፡
በጣም አመሰግናለሁ ጊዜያችሁን ከኔ ጋር ስላጠፋችሁ፡፡

Transcript: Download (234 KB)
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Gosa, Kase
Sheberu, Ejegu
Mamo, Denberu
Tulula, Demesew
Alemu, Tadese
Taye, Hiwot
Bekele, Getnet
Sheberu, Ejegu
Mamo, Denberu
Tulula, Demesew
Alemu, Tadese
Taye, Hiwot
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
- Oral accounts on the development of agriculture in the north-central part of the Lake region
- Types of crops and field technology
- History of livestock production before and after the onset of crop production
- Farming in the revolutionary years
- Interview conducted in Tullure, Lume, East of Modjo town, Lake region, Ethiopia
Date: June 3, 2009
Location: Tullure, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
English
English
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University