Getachew Kasahun and Engeda Kelkele Interview
Audio File:
Download File: Download
Download File: Download
Transcript:
Open/Close
እኔ ፕሮፌሰር ጌትነት በቀለ እባላለሁ የመጣሁት ከአሜሪካን ሀገር ሲሆን የመጣሁትም ጥናት ለማድረግ ነው ስለ አካባቢ አየር ሁኔታ (Environment) የእርሻ የሰብልና የዛፎች ሁኔታ እንዴት ነው ተቀይሯል ወይ? የተቀየረው በምን መልኩ ነው ገበሬዎችን እየጎዳ ነው ወይንስ እየጠቀመ የሚለውን መስተካከል ካለበት እንዴት ነው መስተካከል ያለበት የሚለውን ለማወቅ ጥናት እያደረግን ነው ሌሎችን ነገሮች በመሣሪያ ማጥናት ይቻላል የገበሬዎችን ሃሳብ ግን እነሱን ካላነጋገርን አንችልም ስለዚህ የእናንተን ሃሳብ ለማግኘት ሲሆን ዋናው የምንፈልገው የእዚህን አካባቢ ሁኔታ ቀደም ካለው ጊዜ ጀምሮ አሁን እስካለው ድረስ ለመወያየት ነው፡፡ እኛ ከዛ ላይ ጨምቀን ተለውጧል አልተለወጠም የሚለውን አንድ ወጥ የሆነ ነገር ለማዘጋጀት ስለሚረዳን ነው፡፡
ይህን ያክል ከገለጽኩኝ እናንተም እራሳችሁን እዚህ አካባቢ ምን ያህል እንደኖራችሁ አስተዋውቃችሁኝ ወደ ጥያቄአችን እንገባለን፡፡
1. ጌታቸው ካሳሁን እዚህ አድአ ለ46 ዓመት ኖሬአለሁ
2. እንግዳ ከልክሌ 3ዐ ዓመት ኖሬአለሁ
3. ዳኜ ሀይሌ 18 ዓመት ኖሬአለሁ
ጥ. መሬት እንዴት አገኛችሁ?
መ. በደርግ ጊዜ በ1967 መሬት ላራሹ የተባለ ጊዜ ነው ያገኘነው በውርስም ያገኘ አለ
ጥ. በማሳችሁ ላይ በብዛት የምታመርቱት የሰብል ዓይነት ምንድን ነው?
መ. በዋነኛነት ጤፍ ነው በመቀጠል ስንዴና ሽንብራ ጥራጥሬ በትንሹ ምስር ባቄላ እንዘራለን ሶስቱ ዋና ዋና ናቸው በቆሎም ጓሮ ላይ ይሞከራል፡፡
ጥ. በህይወት ዘመናችሁ ስታስታውሱ የራሳችሁ መሬት ካገኛችሁ ጊዜ ጀምሮ ይህንኑ ነው የምታመርቱት ወይስ የተቀያየረ አዝዕርት አለ?
መ. ከሶስቱ ሌላ ስም ያለው ነገር የምናመርተው የለም እነዚሁኑ አንድ ዓመት አንዱን አንድ ዓመት አንዱን በፈረቃ ነው የምናመርተው፡፡
ጥ. ሁላችሁም እነዚሁኑ ነው የምታመርቱት?
መ. አዎ አካባቢያችን አንድ ስለሆነ ተመሳሳይ ነው የምናመርተው የመጀመሪያ ጤፍ ስንዴ ሽንብራ ነው የምናመርተው፡፡
ጥ. ጤፍን ለምን መረጣችሁት? በአጠቃላይ ዘንድሮ ይህንን ነገር ነው የምናመርተው ብላችሁ የምትሉት? በምን የተነሳ ነው የገበያ ሁኔታ ነው? ለአፈሩ ተስማሚ ስለሆነ ነው ወይንስ ለቀለብ ብላችሁ?
መ. ጤፍ ስንዴና ሽንብራ የምንዘራው በገበያ ላይ ተፈላጊ ነው ጤፍ የገንዘብ ማግኛ ምንጫችን ነው፡፡ ስለዚህ ለገበያም ለቤትም የምንጠቀመው እርሱን ነው መሬቱም ለእነዚህ ሰብሎች ምቹ ነው፡፡ የዚህ አካባቢ ጤፍም በጣም ተፈላጊ ነው ለገበያም ለከብት መኖነትም የጤፍ ገለባ ተመራጭ ነው ፡፡ ስለዚህ ጤፍ ገንዘብ ያስገኝል፣ ቀለብ ፣ ለከብት መኖ ይሆናል፡፡ ስንዘራም ሁሌ አንዳይነት አናመርትም ለመሬቱም ስንል በየዓመቱ እናቀያይረዋለን እንጂ ከጥቅሙ አንጻር ሁሌ ጤፍ እንዘራ ነበር፡፡ የመሬት ጥበትም ስላለ በየዓመቱ እናፈራርቃለን ጤፍ በጣም የሚመረተው የማዳበሪያ ዋጋ የሚሸፈነው በጤፍ ስለሆነ ነው፡፡
ጥ. የአፈር ዓይነቶች 3 አሉ ኮትቻ ጎርበሬና ጨሪ ይባላል ብላችኋል እነዚህም ሶስቱም ለጤፍ ማምረቻ ይሆናሉ?
መ. ይሆናሉ ጥራታቸው ይለያያል ኮትቻው በጣም ጥራት ያለው ጤፍና ምርታማ ነው ወዝ እና በረከት ያለው እህል ነው የኮትቻ ጤፍ፡፡ ሌሎቹም ለጤፍ ይሆናሉ ከኮትቻ መሬት ጤፍ ጋር ግን አይወዳደርም፡፡
ጥ. እነዚህን መሬቶች አፈር ዓይነታችሁ በአይናችሁ አይታችሁ ምን እንደሆኑ ትለዩታላችሁ?
መ. አዎ እንለየዋለን በአካባቢም ይለያያል
ጥ. እስኪ እዚህ አካባቢ ይሄኛው አፈር አለ እዚህ ይሄኛው እያላችሁ ብትነግሩኝ?
መ. አሁን ይሄ ያለንበት ኮትቻ ነው ምስራቅ አካባቢው በደቡብና ምዕራብ አካባቢ ጎንበሬ ሲሆን ጨሪም ጎን ለጎን ነው፡፡
ጥ. ጤፍ እዚህ አካባቢ ከደቡብና ከምዕራብ በተለየ በምሥራቅ አካባቢ በጣም ይመረታል ማለት ነው? ወይስ ሁሉም ያመርታል?
መ. በዚህ ቀበሌ በስተምሥራቅ ያለው ጤፍ ይመረትበታል፡፡ በደቡብና ምዕራብ መሬቱ ጎንበሬ ነው ጥራጥሬዎች ነው የሚመረተው ጤፍም ግን ይመረትበታል፡፡
ጥ. የእናንተ የሶስታችሁ መሬት ምን ላይ ነው ያለው የትኛው መሬት ነው?
መ. ይለያያል እኔ ጨሪ የለኛም ጎምበሬና ኮትቻ ነው ያለኝ፣ የእሱ ደግሞ ኮትቻ ብቻ ነው ሁሉም መሬቱ የእኔ ደግሞ ከሶስቱም አለኝ
ጥ. የእርሻ ቦታችሁ በተለያየ ቦታ ነው ያላችሁ?
መ. አዎ የተለያየ ቦታ ነው ያለን
ጥ. በየቦታው ያለውን መሬታችሁን ደምሩና ስፋቱን ንገሩኝ?
መ. እኔ 3 ሄክታር/ 3ሄክታር ፣ 3.7 ሄክታር
ጥ. የመሬት ጥበት አለ ብላችኋል የርስዎ መሬት ስንት ቢሆን ነው ጥበት መሆኑ የሚቀረው
መ. 6 ሄክታር ባገኝ እንደልቤ መስራት እችላለሁ
ጥ. በናንተ ጊዜ 3 ሄክታር ካነሰ ልጆቻችሁ ምን መሬት ያገኛሉ እስኪ ወደፊት አስቡ ከ3ዐ ዓመት በኋላ ምን መሬት ይኖራል ብላችሁ ታስባላችሁ?
መ. 3ዐ ዓመትማ በጣም ረጅም ነው ለአሁኑ ለአንድና ሁለት ዓመት ስጋት አለን መሬት ፈላጊው ከኛ መሬት ካለን በላይ ነው፡፡ ሥራ አጡ በጣም ብዙ ነው ይሄ ትውልድ ችግር ላይ ነው ያለው እኛም ያንሰናል መሬቱም እየተዳከመ ያለው እረፍት ስለሌለው ነው መሬቱ ሰፊ ቢሆን የተወሰነውን አንድ አራት ዓመት የከብት ግጦሽ ብቻ አድርገነው መሬቱ እራሱን ያክማል አሁን ግን ምንም እረፍት ስለሌለው የመሬቱም ለምነት ጠፍቷል፣ መሬት ቢኖር የተለያዩ ነገሮችን መሞከር ይቻላል፡፡ አሁን ግን ትንሽ ስለሆነ ሌላውን መሞከር አንችልም ከብቶቻችንም ታስረው ነው የሚውሉት የተወሰነ የእህል ዓይነት የምናመርተውም የመሬቱ ጥበት ነው፡፡
ጥ. ሰለከብቶች ትንሽ እናውራ እያንዳንዳችሁ ምን ያህል ከብት አላችሁ?
መ. ምን ይኖራል ያው በዛ ቢባል አንዳንድ ወይፈንና አንድ ላም አንድ ጥማድ በሬ ነው እንዲያውም ለስራ አንድና ሁለት አህያ ይኖራል እኛ ከብት ማደለብም እንፈልጋለን እንሞክራለን ግን የግጦሽ መሬት ስለሌለና የከብት መኖ ስለሌለ እየተቸገርን ነው፡፡
ጥ. የግጦሽ መሬት እዚህ አካባቢ እያነሰና እየጠፋ የመጣው ከመቼ ጀምሮ ይመስላችኋል?
መ. በአፄ ኃ/ስላሴ ጊዜ ነበር የግጦሽ መሬት ያለውም የራሱን አስከብሮ ያበላል የሌለውም ካለው ገዝቶ ያበላ ነበር ለከብቶች መውጫ ቦታም ይተው ነበር እያንዳንዱ ሰው በደርግ ዘመን ለሁሉም ሰው መሬት ሲሰጥ እያነሰ መጣ እየቆየ ሲሄድ እንዳለ እያለቀ መጣ፡፡
ጥ. በጣሊያን ዘመንና ከዛ በፊት ያሉ መረጃዎች እንደሚያስረዱት በድሮ ጊዜ ይሄ አካባቢ በብዛት የከብት እርባታ ይበዛበት ነበር ይባላል? ይሄ መረጃ ትክክል ነው?
መ. አዎ ነበሩ እኛም በትንሹ ደርሰንበታል አንድ ሰው 4 እና 5 ላሞች ነበሩት የእርሻ መሬት ከውጭ አይገዛም ነበር እዚሁ ተወልዶ እዚሁ ይሰጣል እኛ ከቦረና ከአርሲ ነው የምንገዛው፡፡ ከታላላቆቻችን እንደሰማነው ይሄ እንዳለ ጫካ እንደነበርና ከብት ማርቢያ ነበር ይሄ የስምሪት ቦታ ነበር ሲሉ እንሰማለን፡፡
ጥ. ይሄ ጊዜው መቼ ነበር?
መ. በጣሊያን አካባቢ የሚታረሰው መሬት ደን ነበር ይሄ አካባቢ ዋጮ ነበር አውሬ ያስቸግረን ነበር የሚሉ ሰዎች ነበሩ፡፡
ጥ. እዚህ አካባቢ በንጉስ ዘመን የመሬት ስሪቱ እንዴት ነበር?
መ. እዚህ አካባቢ የእርሻ መሬት አልፎ አልፎ ነው አንጂ ጫካ ነበር ከንጉስ ወደዚህ ነው መሬት የተከፋፈለው ስሪቱ የፊውዳላዊ ስርዓት በጣም የተነጋነነበት አካባቢ ነበር አድአ ተብሎ እንደ ሀገር ታዋቂና መሬቱም ለም ስለነበር መሬት እንኳን ሲሰጥ በጣም ታዋቂና ለራሳቸው ቅርበት ያላቸውን ሰዎች ይህንን ግዳጅ ከተወጣህ ከአድአ መሬት ይሰጥሀል ይባል ነበር፡፡ እነሱ የተንሠራፋባት ቦታ ናት ትልልቅ ባለስልጣናት በሙሉ መሬት ነበራቸው እዚህ አካባቢ እነ ራስ መስፍንና የመሳሰሉት መሬት ነበራቸው ሌላው የሚኖረው በነርሱ ስር ሆኖ የነሱን መሬት ጠባቂ በመሆን ነው፡፡
ጥ. በዛን ወቅት ለነሱ መሬት የሚሰጢቸው ንጉሱ ናቸው የሚሰጧቸውስ ከገበሬ ነጥቀው ነው ወይስ ደኑን መንጥረው እንዲያለሙ ነው የሚሰጣቸው?
መ. ድሮ በባላባት ነው አካባቢ የሚመራውና ቦታውን የያዙት እዚህ አካባቢ ያሉ ተወላጆች ናቸው ቦታውም በጣም ሰፋፊና ከጋራ መለስ የአንድ ሰው ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለባላባቱ ነው እንዲሰጥ የሚታዘዘው፡፡
ጥ. የባላባቶቹ ስማቸው ይታወቃል?
መ. አይታወቅም
ጥ. አድአ ማድቤት ነበር ይባላል ምን ለማለት ነው?
መ. ማድቤት ማለት ምግብ የምናገኝበት ነው ስለዚህ ይሄም የእናት ጓዳ ለማለት ከአድአ ሁሉም ነገር ይገኛል ለማለት የተሰጠ ስም ነው፡፡
ጥ. አፄ ኃ/ስላሴ እዚህ አካባቢ እርሻ ነበራቸው ይባላል? እውነት ነው? ካለ ቦታውንስ ታውቁትአላችሁ?
መ. አዎ ሁዳድ ነበራቸው ቦታውም ከደብረዘይት እንስሳት ሕክምና ፋክሊቲ ገባ ብሎ የመንግስት እርሻ የነበረበት ቦታ እዛ አካባቢ የግርማዊት፣ የልዑል አልጋ ወራሽ እየተባለ ሁዳድ ነበራቸው፡፡ ከዚህ አልፎ ሊበንም አላቸው ይባል ነበር፡፡
ጥ. ጣሊያኖች እዚህ ለመስፈር አስበው መሬት መርጠው አርባና ሃምሳ የሚሆን መኖሪያ ቤት ሠርተው የጣሊያን ገበሬዎችን አምጥተው ነበር ይባላል ስለዚህ የምታውቁት አለ?
መ. እንደነበሩ ሰምተናል ምድር ባቡር አካባቢ ደረቅ ጣቢያ አለ እዛ አካባቢ፣ ጎጀኖ የሚባል ቦታም በባቦጋይ አልፎ ያለ ቦታና ኩሪፍቱን አልፎ ያለው ቦታ አካባቢ እንደነበሩ እና አንዳንድ ቅርሳ ቅርሶችም እዛ አካባቢ አሉ እነሱ የሠሩትም መንገድ እዛ አካባቢ አለ፡፡
ጥ. እናንተ በምታውቁበት ዘመን /ጊዜ/ የአየሩ ሁኔታ የዝናቡ መጠን የሚዘንብበት ጊዜ የሙቀት ባጠቃላይ የተቀየረ ነገር አለ?
መ. አዎ ተቀይሯል
ጥ. እንዴት ነው የተቀየረው?
መ. አሁን ለድሮ ሰኔ ክረምት ገባ ነበር የሚባለው አሁን ግን ይሄው መዝነብ የጀመረው ሐምሌ ከገባ ነው ስለዚህ ተቀያይሯል፡፡
ጥ. ይሄ ነገር ያጋጠማችሁ ዘንድሮ ነው ወይንስ ተደጋግሟል?
መ. ተደጋግሟል አንዳንዴ ዘግይቶ ይገባል ወይም ቀድሞ ይቆማል መሬቱም ለምነቱን እያጣ መጥቷል በተደጋጋሚ ያለእረፍተ ይታረሳል ምርት በደንብ እንዲሰጥ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ይረጫል ማዳበሪያው ሰብሉን እንዲዳብር ያደርጋል ሰብሉ ዳበረ ማለት የመሬቱን ምግብ በደንብ ተጠቀመ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በእኛ ዕድሜ ህዳር አጋማሽ ነው ዳር ዳሩን የምናጭድ የነበረው እስከ ታህሳስና ጥር ድረስ አጨዳ ይቆይ ነበር፡፡ አሁን ጥቅምት ላይ ይደርቃል በፊት ያለማዳበሪያ ጥሩ ምርት እናገኝ ነበር፡፡ የፖስታ ስንዴ ዱራሚ ያለማዳበሪያ ነበር የምናመርተው አሁን ያለማዳበሪያ ምንም ማምረት አይቻልም፡፡ ለወደፊቱም ስጋት አለን እንዴት እናመርታለን እያልን እስካሁንም የምንሰራው የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እያደረጉልን ነው፡፡
ጥ. ትክክለኛ ክረምት ነው የምትሉት በዚህ አካባቢ ከመቼ እስከመቼ ነው?
መ. ከሰኔ 24 እስከ መስከረም 24 ነው፡፡
1

Transcript: Download (248 KB)
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Kasahun, Getachew
Kelkele, Engeda
Bekele, Getnet
Kelkele, Engeda
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
- Remarks on the link between soil types and plant growth.
- Local cuisine.
- Distribution of major and minor crops.
- Land shortage and landlessness.
- Interview took place in Ude, just to the south of Debre Zeit town, Lake region, Ethiopia
Date: July 4, 2010
Location: Ude, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University