Mario Bushi, Lansemo Lulo, Tura Harticha, and Elias Gudisa Interview
Audio File:
Download File: Download
Download File: Download
Transcript:
Open/Close
እኔ ፕሮፌሰር ጌትነት በቀለ እባላለሁ
ስማችሁን አስተዋውቃችሁኝ ወደ ጥያቄና መልስ እንገባለን፡፡
1. ዋሪዎ ቡሼ
2. ላንሶሞ አሎሎ ዕድሜ 45
3. ቱራ አርሲቻ ዕድሜ 75
4. ወረዳ አታቻ ዕድሜ 38
5. ኤልያስ ውድሳ ዕድሜ 5ዐ
6. ኑራ ለቡ
የምናደርገው ከድሮ ጀምረን ወደ አሁኑ እንመጣለን የምታውቁትን ትነግሩኛላችሁ ስለድሮውም ስለአሁኑም
ጥ. ከአፄ ምኒልክ ዘመን በፊት እዚህ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የአመጋገብ ሥርዓታቸው እንዴት ነበር ምን ይበላሉ ? ምንስ ይጠጣሉ ? ይህን የሚያውቅ ካለ
መ. ማር ወተት፣ ገንፎ ይመገቡ ነበር በዛን ወቅት ብዙም እርሻ የለም
ጥ. የምን ? ገንፎ ነበር የሚበሉት
መ. የበቆሎና የገብስ ነው በወፍጮም አይፈጭ በዛን ወቅት በእጅ ነበር የሚፈጨው
ጥ. ካላረሱ ገብስና በቆሎ ከየት ይመጣል ?
መ. በቆሎና ገብስ በትንሹም ቢሆን ያመርቱ ነበር
ጥ. በዛን ወቅት አስተዳዳሪያችሁ ማን ነበር ?
መ. አፄ ኃ/ስላሴ ናቸው
ጥ. ከዛ በፊትስ
መ. አናውቅም
ጥ. ቱኬ ማማን የሚያውቅ አለ ወይ ? አስኪ ስለሱ ንገሩኝ
መ. ቱኬ ማማ አስተዳዳሪ ነበር
ጥ. ማን ሾማቸው ?
መ. አፄ ምኒልክ ናቸው
ጥ. ከቱኬ ማማ በፊትስ ማን ያስተዳድር ነበር ?
መ. አፄ ምኒልክ፣ እያሱ፣ ዘውዲቱ
ጥ. እዚህ አካባቢ እርሻ በጣም የተስፋፋው መቼ ነው ?
መ. ከጣሊያን በኋላ በኃ/ስላሴ ጊዜ ነው
ጥ. ምን እህል ነበር በብዛት የሚመረተው ?
መ. በቆሎ፣ባቄላ፣ ገብስ
ጥ. ስንዴስ ?
መ. ስንዴ በቅርብ ነው የተጀመረው
ጥ. በደርግ ነው ስንዴ የመጣው ?
መ. በአፄ ኃ/ስላሴ መጨረሻ አካባቢ
ጥ. ሌላስ ምን ምን እህል አለ ?
መ. ዘንጋዳ፣ ጤፍ አለ ግን በብዛት አንዘራውም
ጥ. ቀደም ባለው ጊዜ እዚህ አካባቢ ከእርሻ ይልቅ ከብት ነው የሚያረቡት ይባላል ትክክል ነው?
መ. አዎ ከብት ነው የሚያረቡት እርሻ በትንሹ ነው ግን ትንሽ ታርሶም በጣም በቂ ነው ከብቶቹ ሳር በደንብ ስለሚያገኙ ወተት ይሰጣሉ ወተትና ቅቤ አለ
ጥ. ከብት መቀነስ የጀመረው መቼ ነው ?
መ. በመንግስቱ ኃይለማርያም ዘመን ነው
ጥ. ለምን ይመስላችኋል ?
መ. ከአፄ ኃ/ስላሴ መጨረሻ ጀምሮ በመንግስቱ ጊዜ ሰው በዛ መሬቱ አለቃ የግጦሽ መሬት ጠፋ፣ የቱኬ ማማ ጭቃ ሹሞች ነበሩ በባላባትነት በዛን ወቅት ይዘው እያሉ ነው ደርግ ገብቶ መሬት ለህዝቡ የተከፋፈለው ሰው በዛ እርሻም በዛ አየሩም አነሰ በጋና ክረምቱ ተቀላቀለ
ጥ. ህዝብ በዛ እያላችሁ ነው ለምንድነው ነው? ህዝብ የበዛው ሰው ብዙ እየወለደ ነው? ወይስ ከሌላ ቦታ እየመጣ
መ. በደርግ ጊዜ ሰው በብዛት ከተለያየ አካባቢ በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም መጣ እነርሱም ይዋለዳሉ በዚህ ምክንያት ነው
ጥ. በደርግና በአፄ ሀ/ስላሴ ጊዜ ያለው የገበሬው ችግር ምንድነው ? በማነፃፀር ቢያቀርቡልኝ
መ. በደርግ ጊዜ መሬት ላራሹ በማለት መሬቱ ሁሉ ተከፋፍሎ ታረሰ ለመሬቱ ምንም አልታሰበም በአፄ ሀ/ስላሴ ጊዜ ርስት የባላባት ነበር በነገሌ ወረዳ በቱኬ ማማ ስር 7 ባላባቶች ነበሩ የመሬት ቁጠባም አልነበር በዛን ወቅት ቤተ ርስት በማለት እስከ 4ዐ ጋሻ ያረሰ አለ፡፡
ጥ. በመንግስቱ ጊዜ ዋናው ችግር ምንድነበር የገበሬው ?
መ. መንግስቱ ኃ/ማርያም ሲመጣ መሬት ላራሹ ሆነ ሁሉም መሬት አገኘ ምንም ችግር የለም
ጥ. እስኪ እርስዎ በግሎ መሬት እንዴት እንዳገኙ በእርስዎ መሬት ላይ በራስዎና በቤተሰብዎ ያገጠመዎት ችግር ካለ ቢገልፁልኝ ?
መ. የኛ ችግር በሁለቱ መንግስታት በአፄ ሀ/ስላሴ የምናርሰው መሬት በባላባቱ ቁጥጥር ስር ሆኖ እኛ ጭሰኛ ሆነን አንሠራ ነበር መሬት በኮንትራት እናገኝና ግብር እንከፍል ነበር፡፡ በመንግስቱ ጊዜ መሬት ለአራሹ ሆነ በባላባት እጅ የነበረ መሬት ከፋፍለው ሰጡን
ጥ. ስንት ጥማድ መሬት ነው ያገኙት
መ. አንድ ሄክታር ነው የተሰጠኝ አሁንም እዛው ላይ ነው ያለሁት?
ጥ. አሁን እርስዎ ያሉበት መሬት የባላበት ነበር ከሆነ ማን ነበር ባላባቱ?
መ. የባላባት ነበር ፊጋ ቤቶ ይባሉ ነበር
ጥ. እርስዎ ለፊጋ ምን ነበር የሚገብሩት ?
መ. እኔ ለፊጋ ምንም አልገበርኩኝም ትንሽ ነበርኩ ለኔ መሬት የተሰጠኝም ደርግ ነው
ጥ. የደርግንና የኢህአዲግን ጊዜ ይውሰዱና በእርስዎ ህይወት ላይ ምንድነው በኑሮዎ በእርሻዎ ያመጣው ለውጥ የትኛው ነው?
መ. በሁለቱም ወቅት ያጋጠመኝ ችግር የለም ደርግ መሬት ለሌለው ሁሉ እንዲደለደል /እንዲያገኝ አደረገ፤ በኢህአዲግ ደግሞ የያዛችሁትን እንደያዛችሁ ተቀመጡ ተባለ ትንሽም ትልቅም ያለው የያዘውን ይዞ ተቀመጠ አሁን ያለው ችግር ከስር ያሉ ልጆች ሲደርሱ ምን ይሆናሉ የሚል ስጋት አለን መሬቱ ስለሌለ፡፡
ጥ. እርስዎ እርሻ ለስንት ዓመታት አረሱ ?
መ. ከ2ዐ ዓመት በላይ
ጥ. በደርግ ጊዜ ግብርና ጀምረዋል ?
መ. አዎ
ጥ. የመሬትዎ ስፋት ስንት ነው?
መ. አንደ ሄክታር
ጥ. መሬትዎ ላይ ምንድነው የሚያርሱት ?
መ. በቆሎ፣ ስንዴና ጤፍ ነው
ጥ. ከብት አለዎት? ካለዎት ስንት?
መ. አዎ ሶስት አለኝ አንድ ላምና አንድ ጥማድ በሬ
ጥ. መሬቱን እንዴት አገኙት? ከቤተሰብ በውርስ ነው ? ወይንስ በደርግ ጊዜ ሲከፋፈል ነው ያገኙት
መ. በደርግ ጊዜ ሲከፋፈል ነው ያገኘሁት
ጥ. አሁን እርስዎ በእርሻዎ ላይ ያለው ከፍተኛ ችግር ምንድን ነው?
መ. የዝናብ እጥረት ነው ያለብን ችግር
ጥ. የዝናብ እጥረቱ ምርቱን አሳንሶታል እስኪ በፊት ከሚያመርቱት ጋር አነፃፅረው ቢነግሩኝ ምን ያህል ስንዴ? ምን ያህል በቆሎ
መ. በፊት በሄክታር ሲዘራ 3ዐ ና 4ዐ በቆሎ ይገኛል ስንዴ በአንድ ጥማድ ሰባትና ስምንት ኩንታል አሁን ግን አራትና አምስት ነው የሚገኘው
ጥ. ማዳበሪያ ተጠቅመው ያውቃሉ?
መ. አዎ ያለማዳበሪያ አይዘራም
ጥ. አሁን ማዳበሪያ ተጠቅመው በአንድ ጥማድ ስንት ኩንታል ስንዴ ነው የሚያገኙት?
መ. አራት ኩንታል
ጥ. በፊት በአንድ ጥማድ ከዚህ የተሻለ ያገኙ ነበር?
መ. አዎ ሰባትና ስምንት ኩንታል ይገኝ ነበር
ጥ. ይሄ ችግር በምን ተከሰተ ብለው ያስባሉ?
መ. የዝናቡ እጥረት ነው
ጥ. ዝናብ ቢኖር እንደ ድሮው ይመረታል ብለው ያስባሉ የመሬቱ ለምነት አልተቀየረም?
መ. አዎ አልተቀየረም መሬቱ ለም ነው
ጥ. እርስዎ እንደዚህ አካባቢ ነዋሪነቶ የአየር ሁኔታው የተቀየረ ይመስልዎታል ለምሳሌ ሙቀት ጨምሯል ወይስ ብርድ ዝናብ በወቅቱ አይመጣም?
መ. አዎ ከኛ በላይ ያለው አካባቢ ደጋ ይሄ ወይና ደጋ ነበር አሁን ግን የኛ ቆላ ሆኗል፡፡
ጥ. ዝናብ መቼ ነበር እዚህ አካባቢ የሚጀምረው?
መ. ሚያዝያ ሲገባ አልፎ አልፎ መጋቢት መጨረሻ ጀምሮ ሚያዝያ ይዘንባል በቆሎ ከሚያዝያ እስከ ግንቦት ይዘራል በመቀጠል ስንዴ ይዘራል
ጥ. ስንዴና ጤፍ መቼ ነው የሚዘራው?
መ. ስንዴ ከሰኔ እስከ ሀምሌ ጤፍ ሀምሌ
ጥ. በቆሎ መቼ ይታጨዳል?
መ. ህዳር ነው
ጥ. እስከዛ ይቆያል?
መ. አዎ
ጥ. ስንዴና ጤፍስ
መ. በጥቅምት
ጥ. ከህዳር እስከ ሚያዝያ ገበሬው ምን ይሰራል?
መ. ያጨደውን ይወቃል እንጂ ምንም ሥራ የለውም በጋ ስለሆነ
ጥ. አሁን የክረምትና የበጋ ዘመን የተቀያየረ ይመስልዎታል?
መ. በዝናብ ስናይ ተቀይሯል
ጥ. በዚህን ወቅት ብዙ መዝነብ ነበረበት?
መ. አዎ አሁን ግን የለም
ጥ. የዝናቡ እጥረት በአሁኑ ዓመት ብቻ ነው የተፈጠረው?
መ. ሶስት ዓመት ሆኖታል
ጥ. የዝናቡ መጥፋት በምን ምክንያት የተፈጠረ ይመስላችኋል ከግብርና ባለሙያዎችስ ጋር ተነጋግራችኋል?
መ. ደን አልቆ ነው ይባላል፡፡ ዝናቡ የሚመጣው ግን ከእግዚአብሔር ነው እሱ እስኪመልሰው መጠበቅ ነው
ጥ. እርስዎስ ስንት አመት አርሰዋል? ገበሬ ከሆኑ ስንት ዓመቶት ነው?
መ. የህፃንነቴ ከተቆጠረ ረጅም ነው የራሴን ማረስ የጀመርኩት ግን ደርግ ገብቶ በ3ኛው ዓመት ነው
ጥ. መሬት እንዴት አገኙ?
መ. ቀበሌ ነው የሰጠኝ
ጥ. አባትዎ ከዛ በፊት አልነበራቸውም?
መ. አባቴ አላቸው እሳቸው ግን እዚህ ወረዳ አይደሉም ከንባታና ሀዲያ አውራጃ ነው ያሉት
ጥ. ደርግ መሬት ላራሹ ብሎ ሲያከፋፍል ነው ያገኙት?
መ. አዎ ደርግ ገብቶ በ4ኛው ዓመት ነው ያገኘሁት
ጥ. ምን ያህል መሬት አገኙ?
መ. ሁለት ተኩል ጥማድ ነበር
ጥ. አሁን ተቀንሷል ወይስ ተጨምሯል?
መ. ተጨምሮልኛል
ጥ. መቼ ነው የተጨመረልዎት?
መ. በ1978
ጥ. በዛው በደርግ ዘመን ነው የተጨመረልዎ ምን ያህል ጥማድ ተጨመረልዎት?
መ. ሁለት ተኩል ተጨምሮልኝ በጠቅላላው አምስት ሆነልኝ
ጥ. ማሳዎት ላይ የሚያርሱት ዋና ምርትዎ ምንድን ነው?
መ. እዚህ አካባቢ ዋና ምርታችን በቆሎ ነው በመቀጠል ስንዴ ሌላ ለማምረት ሰፊ ቦታ ስለሌለን በመጠኑ ነዉ፡፡
ጥ. እርስዎ እርሻ ለምንድነው የሚያርሱት?
መ. ለመኖር ለራሴና ለቤተሰቤ ብዬ
ጥ. ለገበያ ብለው አስበው ያውቃሉ እርሻ ሲወጡ
መ. እራሴንና ቤተሰቤን ከቀለብኩ በኋላ ቤቴን እኔ የምፈልገውንም ለመግዛት /ለልውውጥ/ ነው የምሸጠው
ጥ. ወደ እርሻ ሲወጡ ግን የሚያስቡት እራስዎንና ቤተሰብዎን ለማስተዳደር ነው?
መ. አዎ
ጥ. እቤታችሁ ውስጥ ብዙ ጊዜ የምትመገቡት ምግብ ከበቆሎ የተሠሩ ምግቦችን ነው?
መ. አዎ በአንደኝነት የምንመገው ከአረስነው በቆሎ ነው
ጥ. ከአረሳችሁት ምን ያህል ተርፏችሁ ትሸጣላችሁ በዓመት?
መ. በአሁኑ ወቅት ብዙም ትርፍ የለም ያው ለልውውጥ ያክል ነው የምንሸጠው
ጥ. መጀመሪያ ማዳበሪያ መቼ እንደተጠቀሙ ያስታውሳሉ?
መ. በ1974 ነው
ጥ. የማዳበሪያን ጥቅም ማን አሳየዎት?
መ. የማዳበሪያ ጥቅምን መጀመሪያ ያስተማረን የግብርና ባለሙያ ነው
ጥ. መቼ?
መ. በ1974
ጥ. በደንብ ስለአጠቃቀሙ ተምረዋል ማዳበሪያውስ ጠቅምዎታል?
መ. አዎ ያኔ ጠቅሞኛል
ጥ. እንዴት ?
መ. በፊት ገበሬ ሙሉ በሙሉ ያለማዳበሪያ ነበር የሚጠቀመው ቀስ በቀስ የግብርና ባለሙያ እያስተማረ ህዝቡም ይጠቀም ጀመር ገበሬውም ተማረ ዕውቀትም ሲመጣ ይጠቀም ጀመር፡፡
ጥ. የማዳበሪያ ጥቅም ምንድነው ተብለው ቢጠየቁ ምን ይላሉ?
መ. የማዳበሪያ ጥቅም ምርቱ ከፍ ይላል በባዶ ከሚዘራው የተሻለ ነው
ጥ. ማዳበሪያ ጉዳት ያስከትላልስ ብለው ያስባሉ?
መ. አዎ ጉዳት አለው ጉዳቱም በፊት 35 እና 5ዐ ብር ነበር ገዝተን የምንጠቀመው አሁን 45ዐ ብር ገብቷል አንድ ኩንታል ስንዴና 5ዐ ኪሎ ማዳበሪያ እኩል ነው በገበያ ላይ እኔ 2 ሄክታር አርሳለሁ ብል የምጠቀመው 2ዐዐ ወይም 3ዐዐ ኪሎ ማዳበሪያ ያስፈልጋል ስለዚህ 5 ኬሻ ስንዴ ብሸጥ የምጠቀሙውና የማገኘው የተለያየ ነው ገለባና የተወሰነ ትርፍ ከተገኘ ነው እንጂ እርስ በርስ መቀየር ነው፡፡ ድሮ ግን 4ዐ ና 5ዐ በምንገዛበት ጊዜ አንድ ጥማድ ስንዴ ከ5-6 ኩንታል ይገኝ ነበር ስለዚህ አሁን ብዙ ዋጋ ተከፍሎ ነው ምርት የሚገኘው
ጥ. ይህንን ችግር በምን ምክንያት የመጣ ይመስላችኋል?
መ. በመጀመሪያ ደረጃ አየሩ ተለውጧል፡፡ እዚህ አካባቢ በፊት አንድ ቀን ዝናብ ከዘነበ አስከ 4 እና 5 ቀን ጭቃ ነበር የሚሆነው አሁን መሬቱ አሸዋ ሆኗል፡፡ ጭቃ የለም፣ ዝናቡም በወቅቱ አይመጣም ደረቅ አየር ነው ያለው ዝናብ ከመጋቢት ጀምሮ ይዘንባል በሚያዝያ አርሰን እንጨርስ ነበር አሁን ግን ይሄ የለም፡፡
ጥ. ዝናብ ቢኖር ሌላው ነገር ባይኖርም ጥሩ ምርት ይገኛል ብለው ያምናሉ?
መ. አዎ አምናለሁ ገበሬው አሁን ተምሯል ዝናብ ቢኖር ጥሩ ያርስ ነበር
ጥ. መሬት መቼ እንዳገኙ ቢነግሩኝ?
መ. እኔ መሬት ያገኘሁት መንግስት ሰጥቶኝ አይደለም ከአባቴ በውርስ ነው ያገኘሁት አባቴ በፊት ሲቀበል በባለርስት ስር ይተዳደር ነበር መሬት በደርግ ቁጥጥር ስር ሲሆን የባለርስቱን መሬት አባቴ ወረሰ፡፡ እኔ ደግሞ ከአባቴ ወረስኩ፡፡
አንድ መንግስት ሄዶ ሌላ ሲመጣ ለውጥ አለ በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመን መሬት ነበር ግን አይታረስም በትክክል ማረስ የጀመርኩት በኢህአዲግ ዘመን ነው 5 ጥማድ መሬት አለኝ ገብስ በቆሎ ስንዴ እዘራለሁ ሌላውን እንዳልዘራ የመሬት ስፋት ያንሰኛል
ጥ. በአንደኛ ደረጃ ስንዴ ከዛ በቆሎ ነው የሚያርሱት?
መ. ከሚያዝያ እስከ ሰኔ በቆሎ እያልን በየተራና በየወቅቱ ስንዴ እያልን በመቀጠል እንዘራለን ማዳበሪያ በደርግ ጊዜ ደርግ ድጎማ እየከፈለ ይሰጠን ነበር ገበሬም በዚህ ይጠቀም ነበር አሁን ግን በነጋዴ እጅ ስለገባ ማዳበሪያው በጣም ተወደደ መሬቱ ማዳበሪያ ስለለመደ በኮምፖስም መጠቀም አልቻልንም ስለዚህ በጣም ችግር አለ የምግብ እጥረት ሁሉ አንድ ሰው የሚሰራው ለመብላት፣ ለመኖር ለመማር በመሆኑ ብዙ ወጪዎች አሉ የሰው ብዛትና የመሬት እጥረት አለ፡፡ የገበያውንም ሁኔታ ስናይ ማዳበሪያ በቆሎና ስንዴ ዋጋው አንድ ሆኑ ከዚህ በተጨማሪ የአየር መዛባት ያስከተለው ችግር ነው ይህም ከሆነ ከ3 ዓመት በላይ ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያት አንድ መሬት ሰባት እና ስምንት ኩንታል የሚወጣው በአየሩ መዛባት ሶስት እና አራት ኩንታል ብቻ ይመረታል፡፡
ጥ. ድጎማን በተመለከተ ከፍተኛ ባለስልጣኖችን አነጋግረን ነበር እነሱ የሚሉት ገበሬዎች የእህል ዋጋ ስለጨመረ ያለ ድጎማ ማዳበሪያ መግዛት ይችላሉ? የላሉ ይህን እንዴት ታዩታላችሁ?
መ. ያንን መወሰን የምንችለው ዋጋው ከፍ ዝቅ ሲል ነው የምንኖረው በአቅም ስለሆነ ይሄ ትክክል አይደለም እኛ አቅም ስለሌለን መንግስት ድጎማ አድርጎ ቢያቀርብ ጥሩ ነው፡፡
ጥ. ከመንግስት ሃላፊዎች ጋር ስንነጋገር የመሬት የባለቤትነት ጉዳይ አለ መሬት ግን የማን ነው? መሸጥ መለወጥስ ትችላላችሁ
መ. መሬት በፊት በግለሰብ እጅ ወይም በባለርስት እጅ ነበረች አሁን ግን መሬት የመንግስት ነው ተብሏል ኘላኑ ወጥቶለት ግን ለእያንዳንዳችን ተሰጥቶናል፡፡ መሸጥ መለወጥ ግን አንችልም
ጥ. እርስዎ አሁን መሬትዎን ቢሸጡ ቢለውጡ ደስ ይሎታል?
መ. እኔ መሸጥን አልወድም አልፈልግምም
ጥ. የከተማ ሰዎች መሬት ቆርሰው ይሸጣሉ አንደገና ይገዛሉ እርስዎ ይህንን ይደግፋሉ?
መ. በእርግጥ ይህንን እኔም አልደግፈውም የከተማ መሬት ከፍያለ ጥቅም ሊኖረው ይችላል እኔ ግን አልሸጥም ገንዘብ አላቂ ነው፡፡ መሬት ለባለቤቱ እንደሚስት ነው፡፡ ሚስት አትሸጥም
ጥ. በደርግ ጊዜ መሬት እንደምንሰማው ከሆነ በየሁለት ዓመት እየለካ እንደገና ያከፋፍላል አሁን ይሄ ይደረጋል ወይ?
መ. የለም
ጥ. አሁን በኢህአዲግ ዘመን የገበሬ ችግር ምንድን ነው?
መ. በዕድሜዬ በአፄ ኃ/ስላሴ 17 ዓመት አርሻለሁ 17 ጥማድ እያረስኩ ግብርም ከፍያለው በደርግም 17 ዓመት አርሻለሁ በሀይለስላሴ መሬት ለምና ስፋት ነበራት በኋላ ገመድ ገባ
ጥ. ገመድ የገባው የተለካው መቼ ነው?
መ. በባለርስት ነው ጋሻ እየተባለ ገመድ የገባ
ጥ. ቅፅል ስሙ ሽቦ የሚገባል ሰው ያውቃሉ ወይ?
መ. ሽቦ ተጣለ ሲባል ታሪክ እናውቃለን ሰውየውን አናውቅም ለአንድ ሰው ነው 5 እና 4 ጋሻ የሚያሳርሰው የሚታረሰው አሁን ሰው በዛ ሁሉም ነገርም ተወደደ ደርግ እንደመጣም መሬት ለአራሹ ተብሎ ተወረሰ ያን ዘመን በቤተሰብ ልክ ነው መሬት የሚከፋፈለው በቤተሰብ ቁጥር ነው 12 ቤተሰብ ያለው ሰው አንድ አንድ ጥማድ የተከፋፈለ ግን አነሰን ስንከፋፈል ደስ ብሎን ነበር ግን ግብርና ኮታ ጫኑብን በዘመኑ አንድ ልጅ ያለውን ግምባር ለጦርነት ይልክ ነበር በግዳጅ እሱም ሄደ ይሄ መንግስት ገባ መሬቱም ትልቅም ይሁን ትንሽ እንደያዝን ቀረን፡፡
መሬት አትሸጥም አትለወጥም የመንግስት ናት ስለተባለ የራሴ እስከሆነ ለምን የፈለግነው አናደርግም ለምን ይህንን አስቀመጡብን የራሴን እንደፈለኩ ለምን አላደርግ ኘላን አስነሱ ተብለን አስነስተን ኘላኑም በእጃችን ነው በርግጥ መሬት መሸጥ የለበትም የከተማ ሁኔታ የቆዳ ስፋትም ስላለ ካሳ ተቀብለው ለማዘጋጃ ቢሸጥ ማንም እየከላከለው አይደለም፡፡ አሁን ማዳበሪያ ሲወደድ ከሰው ብዛት ነው ወይንስ ምንድነው እያልን እንጨነቃለን ማዳበሪያ በጣም ተወዷል ነጋዴ እጅ ገብቶ ማዳበሪያ በመንግስት እጅ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
ጥ. አሁን አንድ ሀይል መጥቶ የገበሬዎችን ችግራችሁን ልፈታላችሁ እችላለሁ የምፈታላችሁ ግን ከችግሮቻችሁ መሀል አንድ ችግር ብቻ ነው ቢላችሁ የምታስቀድሙት ችግራችሁ ምንን ነው?
መ. ይህንን የጠየቃችሁት ችግራችንን ልትፈቱ ከሆነ መንግስት ገበሬውን ማዕከል አድርጌ እሰራለሁ ነው የሚለው ግን ምንም አልተደረገልንም ከህዝቡ 85% ገበሬ ሆኖ ምንም የተደረገለት የለም ዘንድሮ ገበሬው እንዳለ የዘራው በብድር ነው መንግስትም አይቶ ምንም አላደረገም ገበሬው ከመንግስት የማዳበሪያ ወይም የገንዘብ ድጎማ ቢደረግ ለውጥ ይመጣል፡፡
ገበሬው ተለውጧል የሚባለው ካለው ገበሬ ከመቶ ሁለት አይሆንም፡፡ አሁንም ሲሸለሙ የምናያቸው ቀደም ባለው ጊዜ ደህና ቅርስ የነበራቸውም ከብትም የነበራቸው ናቸው እንጂ አሁን የተነሱት አይደሉም፡፡
ጥ. ይሄ ሀሳብ የሁላችሁም ነው?
መ. አዎ ሃሳቡ የሁላችንም ነው ድጎማ እንዲደረግልን እንፈልጋለን፡፡
እኛም የምናምነው 85% የሚሆነውን ገበሬ ትተን 15% ብቻ ይዘን እናድጋለን ብንል የትም አያደርሰንም ስለዚህ አብረን ማደግ አለብን አብረን ካላደግን አብረን ነው የምንወድቀዉ ስህተታችንን አውቀን ከዛ በመነሳት ሠርተን ለውጥ ለማምጣት ነው በእርግጥ ለውጥ በቀላሉ አይመጣም፡፡ መንግስት የእህል ዋጋ ላይ ገንዘብ ለመጨመር ከ1ዐ ዓመት በላይ ነው የፈጀው ስለዚህ ጥናታችንም እነዚህን የመሰሉ ሃሳቦችን በመሰብሰብ ለመሻሻል ነው የምንሠራው
አመሰግናለሁ፡፡
1

Transcript: Download (225 KB)
Courtesy of Getnet Bekele
Creator: Bushi, Mario
Lulo, Lansemo
Harticha, Tura
Gudisa, Elias
Bekele, Getnet
Lulo, Lansemo
Harticha, Tura
Gudisa, Elias
Bekele, Getnet
Contributing Institutions: Getnet Bekele, MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University
Description:
- History of the area’s agriculture since the late nineteenth century.
- Farmers’ perceptions about climate change.
- History of fertilizer use.
- Remarks on local and state administration in the contemporary period.
- Land tenure issues in the post-1975.
- Interview conducted in Ali Wayoo, just north of Arsi Nagelle town, Lake region, Ethiopia
Date: July 30, 2010
Location: Ali Wayao, Ethiopia
Format: Audio/mp3
Language: Amharic
Oromo
Oromo
Rights Management: For educational use only.
Digitizer: MATRIX: The Center for Humane Arts, Letters and Social Sciences Online at Michigan State University